1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቻርልስ ቴይለርና የእሥራቱ ቅጣት

ሐሙስ፣ ግንቦት 23 2004

ዴን ኻግ ኔዘርላንድስ የሚገኘው የሲየራ ልዮን ጦር ወንጀልን የሚመለከተው የተመ ፍርድ ቤት በጦር ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው በተገኙት በቀድሞው የላይቤርያ ፕሬዚደንት ቻርልስ ቴይለር ላይ በዛሬው ዕለት የሀምሣ ዓመት የእሥራት ቅጣት በየነ።

https://p.dw.com/p/154c3
Former Liberian President Charles Taylor waits for the start of his sentencing judgement in the courtroom of the Special Court for Sierra Leone(SCSL) in Leidschendam, near The Hague, Netherlands, Wednesday May 30, 2012. The SCSL found Taylor guilty last month on 11 charges of aiding and abetting the rebels who went on a bloody rampage during the decade-long war that ended in 2002 with more than 50,000 dead. Taylor became the first former head of state convicted by an international war crimes court since World War II. Taylor will serve his sentence in a British prison. (Foto:Toussaint Kluiters, Pool/AP/dapd)
ምስል AP

ፍርድ ቤቱ  ባለፈው ወር ነበር ቴይለርን በዘጠነኛዎቹ ዓመታት የሲየራ ልዮን የተባበረው ዓብዮታዊ ግንባር ዓማፅያንን ረድተዋል በሚል ጥፋተኛ ናቸው ሲል ብይን ያሳለፈው። ጥፋተኛ እንዳልሆኑ ያስታወቁት የስድሳ አራት ዓመቱ ቻርልስ ቴይለር በብይኑ አንጻር ይግባኝ ሳይሉ እንደማይቀሩ ይጠበቃል።

« ሚስተር ቴይለር፡ በሚቀጥሉት ምክንያቶች ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ ሆነው በተገኙባችው ወንጀሎች በሀምሣ ዓመት እሥራት እንዲቀጡ በአንድ ድምፅ በይኖዋል። ብይኑ ተይዘው ከታሰሩበት እአአ ከመጋቢት 2006 ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል። »
ዳኛው ሪቻርድ ሉሲክ የእሥራቱን ቅጣት ይፋ ባደረጉበትና ያጠፋ ሁሉ በሕግ እንደሚጠየቅ ባስታወቁበት ጊዜ ያሰሙትን ብይን ነበር ያዳመጣችሁት።

ከሁለተኛ ዓለም ጦርነት ፍፃሜ በኋላ በናዚ ባለሥልጣናት አንጻር ከተካሄደው ችሎት በኋላ  አንድ የሀገር መሪ በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ብይን ሲተላለፍበት የቀድሞው የላይቤሪያ ፕሬዚደንት ቻርልስ ቴይለር የመጀመሪያው ናቸው። ቴይለር እአአ በ  2002  ዓም ባበቃው የሲየራ ልዮን የርስ በርስ ጦርነት ወቅት እጅና እግር በመቁረጥ የጭካኔ ተግባራቸው ይታወቁ የነበሩትን የተባበረው ዓብዮታዊ ግንባር ዓማፅያንን ረድተዋል በሚል ተከሰው እአአ በ 2006 ዓም በስደት ይኖሩባት ከነበረችው ናይጀሪያ ተይዘው በሲየራ ልዮን ወደተቋቋመው የተመድ ጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት ተወሰዱ፤  የርሳቸው የፍርድ ሂደት በሲየራ ልዮን የሚካሄድበት ድርጊት ግን ያካባባውን መረጋጋት ያደፈርሳል በሚል ስጋት ችሎታቸው ወደ ዴን ኻግ ከተዛወረ በኋላ ፍርድ ቤቱ ባለፈው ወር ቴይለርን በአሥራ አንድ የክስ ወንጀልዎች ጥፋተኛ ሆነ አግኝቶዋቸዋል። በዛሬው ዕለትም የሀምሳ ዓመት እሥራት በይኖባቸዋል። በዘጠነኛዎቹ ዓመታት ከነበሩት ጨካኝ የጦር ባላባቶች መካከል አንዱ የሚባሉት የስድሳ አራት ዓመቱ ቻርልስ ቴይለርን ችሎት ካለፉት ስድስት ዓመታት ወዲህ ሲከታተሉ የቆዩት ኦፕን ሶሳይቲ ጃስቲስ ኢኒሺየቲቭ የተባለው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን መሪ ጠበቃው የሲየራ ልዮኑ ተወላጅ አልፋ ሴሴይ  ብይኑ አስደሳችና ለሌሎችም መቀጣጫ ሆኖ እንዳገኙት ገልጸዋል።
« ወሳኝ ወቅት ነው፤ ብይኑ ቅር የሚያሰኝ አይደለም፤ ብዙዎቹ የሲየራ ልዮን የጦር ወንጀል ሰለባዎች ቻርልስ ቴይለር ዕድሜ ይፍታህ እንዲፈረዱ ነበር የጠበቁትና ይህ ደግሞ የዕድሜ ልክ እሥራት ነው። እርግጥ ይህ በሲየራ ልዮን የርስ በርስ ጦርነት ወቅት የተፈጸመውን የጦር ወንጀል ሁሉ ያበቃል ማለት አይደለም። ግን የሕግ የበላይነት እንደሚከበር፡ በተለይም ዳኛው እንዳስታወቁት፡ እንደ ቴይለር ትልቅ ሥልጣን ያላቸው ሰዎችም ሳይቀሩ ለፍርድ እንደሚቀርቡ ያሳያ ወሳኝ ምልክት አስተላልፎዋል። »
በሲየራ ልዮን የተቋቋመው የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት ቃል አቀባይ ፒተር አንደርስም የፍርድ ቤቱን ብይን እንደ ትልቅ ስኬት ነው የተመለከቱት።»
« በዚህና በሌሎች አካባቢዎች  ትልቅ ሥልጣን ያለህ ሰው ከሆንክ በፍርድ ፊት የማትጠየቅበት ጊዜ ነበር። እና ልዩው ፍርድ ቤት በፍፁም አይነኩም ተብለው ይታሰቡ የነበሩ ሰዎችን በከሰሰበት ድርጊቱ ማንም በሕግ ሊቀጣ እንደሚችል ዋነኛ ርምጃ ወስዶዋል።
እአአ ከ 1991  እስከ 2002 ዓም በቆየው የርስበርስ ጦርነት ወደአንድ መቶ ሀያ ሺህ ሰው ሲገደል፡ በዚሁ ጊዜ የተባበረው ዓብዮታዊ ግንባር ዓማፅያን በፈፀሙት ዘግናኙ የእጅና እግር መቁረጥወንጀል ከአምስት ሺህ የሚበልጥ ሰው ሰላባ ሲሆኑ፡ ብዙ ሴቶችም ባማፅያኑ መደፈራቸው ይታወቃል።
 የዛሬውን የፍርድ ቤት ብይን በሲየራ ልዮን መዲና ሊብረቪል በቀጥታ በቴሌቪዥን ከተከታተሉት ሰለባዎች አንዱ የቀኝ እጁ የተቆረጠው አሊማሚ ካኑ በብይኑ እጅግ መደሰቱን፡ የግራ እግሯን ያጡት ሲያህ ሊቢ ደግሞ የዛሬው ብይን መጥፎ ስራ ለመስራት ለተዘጋጁ ሁሉ ጥሩ ማስጠንቀቂያ እንደሚሆን ገልጸዋል።
እርግጥ ፍርድ ቤቱ በቴይለርና ረዱዋቸው በተባሉት የዓብዮታዊ ግንባር ዓማፅያን  መሪዎች ላይ የቅጣት ብይን ማስተላለፉ የመጀመሪያ ርምጃ ቢሆንም፡ አሁንም ብዙዎቹ የጦር ወንጀለኞች  በሲየራ ልዮን ክስ ሳይመሰረትባቸው በነፃ በመዘዋወር ላይ መገኘታቸው ፡ ምንም እንኳን ጦርነቱ ቢያበቃም አሁንም ኑሮዋቸውን የመግፋት ችግር ያልተለያቸውን ያማፅያኑ ወንጀል ሰለባዎችን ቅር ማሰኘቱ አልቀረም።

ARCHIV - Zwei beinamputierte Jugendliche spielen am Strand von Freetown in Sierra Leone mit Hilfe ihrer Krücken Fußball (Archivfoto vom 06.04.2006). Sie zählen zu den Opfern des Bürgerkriegs in Sierra Leone. Fünf Jahre nach dem Ende des Bürgerkriegs muss sich nun der ehemalige Präsident von Liberia, Charles Taylor, vor dem Sondergerichtshof für Sierra Leone verantworten. Aus Sicherheitsgründen wurde der Prozess allerdings ins niederländische Den Haag in die Räume des Internationalen Strafgerichtshofs verlegt. Taylor werden unter anderem Kriegsverbrechen und Verbrechen gegen die Menschlichkeit in der Zeit des Bürgerkriegs in Sierra Leone vorgeworfen. Mit einem Urteil wird frühestens nach anderthalb Jahren gerechnet. Foto: Nic Bothma dpa (zu dpa-Reportage: "Amputierte Kriegsopfer in Sierra Leone ungerührt von Taylor-Prozess" vom 04.06.2007) +++(c) dpa - Bildfunk+++
ምስል picture-alliance/dpa
epa02569790 Former Liberian President Charles Taylor awaits the start of the prosecution's closing arguments during his trial at the U.N.-backed Special Court for Sierra Leone in Leidschendam, Netherlands, 8 February 2011. Taylor denies all 11 charges of instigating murder, rape, mutilation, sexual slavery and conscription of child soldiers during wars in Liberia and Sierra Leone in which more than 250,000 were killed. EPA/Jerry Lampen/POOL
ምስል picture-alliance/dpa

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ