«ቻርሊ ኤብዶ» በሙስሊሙ ዓለም ቁጣ ቀሰቀሰ
ቅዳሜ፣ ጥር 9 2007ከሟቾቹ መኻከል አንደኛው ፖሊስ እንደሆነ ተገልጧል። በጥቃቱ 45 ሰዎች መቁሰላቸዉም ተመልክቷል። በኒጀር ከፍተኛ ተቃዉሞ ከተካሄደ ከአንድ ቀን በኋላ ቅዳሜ ጥር 9 ቀን 2007 ዓም መዲና ኒያሚ ላይ ዳግም ከፍተኛ ተቃዉሞ መደረጉ ተጠቅሷል። መዲና ኒያሚ በሚገኘዉ አንድ ትልቅ መስጊድ አካባቢ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች የሚያደርጉትን ከፍተኛ ተቃዉሞ ለመበተን የፀጥታ አስከባሪ ፖሊስ አስለቃሽ ጋዝ መጠቀሙም ተመልክቷል። ይህ የተቃዉሞ ሰልፍ እንዳይደረግ የባለሥልጣን መሥሪያ ቤቶች ቀደም ሲል አግደዉ ነበር። በኒጀር የሚገኘዉ የፈረንሳይ ኤንባሲ ፈረንሳዉያን ከቤታቸዉ እንዳይወጡ ማስጠንቀቁም ተመልክቷል።
ፓኪስታን ካራቺ ከተማ የሚገኙ ሙስሊም እምነት ተከታዮች በፈረንሳይ ኤንባሲ ላይ ጥቃት ጥለዉ ሦስት ሰዎች መጎዳታቸዉም ተገልጾአል። በዮርዳኖስ እና በአልጀርያ መዲኖች ኦማን እና አልጀርስ ዉስጥ ታላቅ የተቃዉሞ ሰልፍ እንደነበርም ተያይዞ ተመልክቷል። በእስራኤል እየሩሳሌም ጽዮን ተራራ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ተሰብስበዉ ተቃዉሟቸዉን አሳይተዋል። የፈረንሣዩ «ቻርሊ ኤብዶ» በድጋሚ ያወጣው የነብዩ መሐመድ ምስል የሚያነባ ሲሆን፦ «እኔም ሻርሊ ነኝ» የሚል ፅሑፍ አለው። «እኔም ሻርሊ ነኝ» የሚለው መፈክር ፈረንሣይ መዲና ፓሪስ ውስጥ በእስልምና አክራሪዎች ለተገደሉት 12ቱ ሰዎች አጋርነትን ለማሳየት የተሰራጨ እንደሆነ ይነገራል።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ