1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትዝታ፣ ህይወት ወይስ ምስጥ

ሐሙስ፣ መስከረም 20 2003

ህይወት እና ተስፋ ምኞት እና እዉነታ ስራና አጋጣሚ ኑሮና እጣ ፈንታ መንፈስና ስጋ የተዋጉ ለታ አልፎ የሚያጌጡበት ጥበብ ነዉ ትዝታ!

https://p.dw.com/p/PQ8R
ምስል picture-alliance / dpa


ሰሞኑን ኢትዮጽያዉያን እንጋፋና ወጣት ከያኒያን ተሰባስበዉ ያወጡት የትዝታዎች ትዝታ የተሰኘ የሙዚቃ አልብም ላይ ያገኘወነዉ የትዝታ ትርጉም ነዉ! ጤና ይስጥልኝ አድማጮች ትዝታ ከባህል ቅኝታችን አንዱ ነዉ። ትዝታ በትርጉሙ በአንዳንዶች ስርስር የአድርጎ የሚበላ ምስጥም ነዉ!ትዝታ ዳገት ቁልቁለት መዉጫ፣ የሃሳብ መኪናም ነዉ! ሌላም ሌላም የዛሪዉ መሰናዶአችን ከትዝታ ጋር ትዝታን ይዘን ትዝታን ከሚጫወቱልን ትዝታን ከሚገጥሙልን በትዝታ አብረን እንቆያለን ለቅንብሩ አዜብ ታደሰ ነኝ መልካም ቆይታ።


ሰሞኑን ለሙዚቃ አፍቃሪ ከወጣዉ አልብም ሚካኤል በላይነህ የተጫወተዉ ሙዚቃ ነበር ያደመጥነዉ ሰሞኑን ለሙዚቃ አፍቃሪዎች የቀረበዉ አልብም የሶስት ትዉልድ ድምጻዉያን በትዝታ ሰንሰለት ተያይዘዉ ይህን ታሪካዊ አልብም የትዝታዎች ሁሉ ቁንጮ አደረጉት ይላል አድማጮቹን በትዝታ ታንኩዋ ተሳፍረዉ በሙዚቃ ባህር ተንሳፋዉ እፈለጉበት እንዲደርሱ ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ ደግሞ ትዝታን ለየት አድርጎ አቅርቦአት ተወዳጅነትዋ በተለያዩ ድረ-ገጾች እና የብዙሃን መገናኛዎች ተደማጭነትቱ ጎላ ብሎአል እና ምናልባት በትዝታ ላይ አብዮት አድርገህ ይሆን ጥቃቄ ነበር ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ