ትምባሆን የሚመለከተው አዲስ ህግ
ዓርብ፣ የካቲት 25 2008ማስታወቂያ
ስለዚሁ ህግ ምንነት በኢትዮጵያ፣ ምግብ መድሃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን የህግ ዝግጅት ክፍል ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ አብረኸት ግደይ ገልጸውልናል።
ህዝብ በተሰበሰበበት ቦታ ትምባሆ ሲያጨስ የተገኘ ሰውን ወይም እንዲጨስ የፈቀደ ተቋም ህጉን ሳያከብር ቢቀር ቁጣቱ ምንድን ነው? የህግ ባለሙያዋ ወ/ሮ አብረኸት ፤ ይህ እንደየ ክልሉ እና የማስፈፀሚያ ህኑ ይለያያል ይላሉ። ህዝብ በተሰበሰበበት ቦታ ትምባሆ ማጨስን ወይም እንደ አንድ ተቋም ሌሎች እንዲያጨሱ መፍቀድን ስለሚከለክለው ህግ ይህን ያህል ከሰማን፤ ተግባራዊ ማድረግ የሚጠበቅበት ማህበረሰብስ በዚህ ላይ ምን አስተያየት አለው? የጥቂት ወጣቶችን አስተያየት አሰባስበናል።
ሙሉውን ዝግጅት በድምፅ ያገኙታል።
ልደት አበበ
አርያም ተክሌ