ኢትዮጵያዊዉ ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ቴዲ አፍሮ በመግቢያችን ላይ እንዳል ነዉ የስድስት አመት ፅኑ እስራትና የአስራ-ስምንት ሺሕ ብር ቅጣት ተበይኖበታል።ዛሬ ያስቻለዉ የከፍተኛዉ ፍርድ ቤት የመሐል ዳኛ ብዩኑን የሰጡት ድምፃዊዉን በችሎት መዳፈር ከወቀሱት በሕዋላ ነዉ።የአዲስ አበባ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉን ሥለ ፍርድ ሒደቱ ጠይቄዉ ነበር።የአዲስ አበባ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉን በስልክ አነጋግረነዋል።