ለታዳሽ የኃይል ምንጭነት ከሸነኮራ አገዳ በተጨማሪ የማሽላና የበቆሎ አገዳዎች፤ እንዲሁም የጉሎ ዛፍ፤ ጃትሮፋ የተባለዉ ተክልና የዘንባባ ዛፍም ይዉላሉ። ከእነሱ የሚገኘዉም ፍሳሽ መሆኑን ባለሙያዉ አቶ መልስ ተካ አስረድተዋል። ኢትዮጵያ በዋናነት ይህን የታዳሽ ኃይል ለመጠቀም ያለመችዉ አንድም ለነዳጅ የሚወጣዉን የዉጭ ምንዛሪ ለመቆጠብ፤ አማራጭ የኃይል ምንጭ ለማጠናከርና ብክለትንም ለመከላከል ነዉ።