ታዋቂው የጀርመን ደራሲ ኅልፈት
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 6 2007ማስታወቂያ
የዛሬ ሦስት ዓመት « መነገር ያለበት» ሲል SüddeutscheZeitung በተሰኘው ጋዜጣ ላይ በጀርመንኛ ያቀረበው ግጥም እጅግ ከፍተኛ ውዝግብ አስነስቶ ነበር። «በብዕር ቀለሜ ጠብታ ፍፃሜ፥ በስተርጅናው ዘመኔ፥ መነገር ያለበትን ለወገኔ» በማለት የእስራኤል እና የኢራን የኑክሌር ይዞታን በማነፃጸር ትችታዊ ስንኝ ቋጥሮ ነበር። በዚህ ጽሑፉ በወቅቱ «ጸረ-ሴማዊ» በሚል ከፍተኛ ነቀፌታ ደርሶበታል። ከዚህ ዓለም ከተለየ ዛሬ አንድ ቀን አስቆጥሯል። ስለ ደራሲ ጉይንተር ግራስ ሕይወት እና ኅልፈት ሜኽትሂልድ ሜስከር ያዘጋጀውን ይልማ ኃይለሚካኤል እንዲህ ያቀርበዋል።
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማጫወቻ ይጫኑ።
ሜኽትሂልድ ሜስከር /ይልማ ኃይለሚካኤል
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አርያም ተክሌ