ቱሪዝምና ችግሮቹ በኢትዮጵያ
ሐሙስ፣ ግንቦት 15 2005ማስታወቂያ
ጭስ አልባው ኢንዱስትሪ በመባል የሚታወቀው ቱሪዝም የበርካታ አገራት ዋነኛ የኤኮኖሚ መሰረት ነው ። ከአፍሪቃ እንኳን ኬንያ ታንዛኒያ ና ደቡብ አፍሪቃ የዘርፉ ተጠቃሚ ናቸው ። አገር ጎብኝዎችን የሚስቡ ባሃላዊ ታሪካዊና ተፈጥሮአዊ ሃብቶች ያሏት ኢትዮጵያ ግን ከዘረፉ ማግኘት የሚገባትን ያህል ተጠቃሚ መሆን አልቻለችም ። ኢትዮጵያ እንደ ሌሎች የአፍሪቃ ሃገሮች የአገር ጎብኝዎች መስህብ መሆኗን ለማስተዋወቅና የጉዞ ወኪሎችና አስጎብኝዎችም ኢትዮጵያን በፕሮግራማቸው እንዲያካትቱ ለማሳሰብ ፓሪስ ፈረንሳይ ውስጥ ውይይት ተካሂዶ ነበር ። በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የጉዞ ወኪሎችና አስጎብኚ ድርጅቶች በተሳተፉበት በዚሁ ውይይት ላይ በኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ የሚታዩ ችግሮች ተነስተዋል ። ውይይቱን የተከታተለችው የፓሪሷ ወኪላችን ሃይማኖት ጥሩነህ ቀጣዩን ዘገባ ልካልናለች
ሃይማኖት ጥሩነህ
ሂሩት መለሰ
ሸዋዮ ለገሠ