ተጠናክሮ የቀጠለው የዩክሬይን ውዝግብ
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 1 2006ማስታወቂያ
ከሀያ ቀናት በፊት በዚያን ጊዜ የአውሮጳ ህብረት ፕሬዚደንት በነበረችው በሊትዌንያ መዲና ቪልኒዩስ በተካሄደው የአውሮጳ ህብረት እና የምሥራቃዊ አውሮጳ ሀገራት የጋራ ጉባዔ ላይ ይፈረማል ተብሎ የተጠበቀውን የዩክሬይን እና የህብረቱን የፖለቲካ እና የንግድ ትብብር ስምምነት ፕሬዚደንት ያኑኮቪች ባለመፈረማቸው ነበር ተቃውሞው የተነሳው። ይኸው ሁኔታ ዩክሬይንን ወደ ከፋ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ እንዳይጥላት በርካታ የዓለም መሪዎች እና ዲፕሎማቶች ስጋታቸውን እየገለጹ ነው።
ገበያው ንጉሤ
አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ