1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተዘዋዋሪ ገንዘብ ለስራ ፈጠራ

እሑድ፣ የካቲት 12 2009

የወጣቶችን የስራ ዕድል ፈጠራ ለማበረታታት፣ ማለትም፣ ወጣቶች በቀላሉ ብድር ማግኘት የሚችሉበትን 10 ቢሊየን ብር  የያዘ የወጣቶች የዕድገትና ልማት ተዘዋዋሪ ገንዘብ  ባለፈው ሳምንት ይፋ አድርጓል። የዚሁ አዲስ እቅድ አፈጻጸም ሂደት እንዴትነት እና በገሀድ የሚኖረው ትርጓሜ ምን ይመስላል?

https://p.dw.com/p/2Xmn9
MStudenten auf dem Campus der Universität Addis Abeba
ምስል DW

ካለፉት 10 ዓመታት በላይ የወጣቶችን ችግር ለማቃለል መንግሥት ለገጠሩ እና ለከተማ ይበጃሉ ያላቸውን ፖሊሲዎች፣ ስልቶች እና የልማት እቅዶችን አዘጋጅቶ ተንቀሳቅሷል። ፖሊሲዎቹ በዋነኛነት በሃገሪቱ  የሚታየውን የወጣቶች ስራ አጥነት ችግር የማስወገድ እና ወጣቱን በሁሉም ዘርፎች ተሳታፊ የማድረግ ዓላማ ነው ያላቸው። የተጠበቀውን  ያህል ውጤታማ አልሆነም በሚል የተለያዩ አስተያየቶች ነው የሚሰሙት። መንግሥት ለወጣቶች ልዩ ትኩረት በመስጠት የስራ ዕድል ፈጠራን ለማበረታታት፣ ማለትም፣ ወጣቶች በቀላሉ ብድር ማግኘት የሚችሉበትን 10 ቢሊየን ብር  የያዘ የወጣቶች የዕድገትና ልማት ተዘዋዋሪ ፈንድ ባለፈው ሳምንት ይፋ አድርጓል። ከዚሁ ለተዘዋዋሪው ፈንድ ከተመደበው ገንዘብ መካከል የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር 5 ቢሊየን ብሩ ወደ ባንክ ማስገባቱ ተገልጿል። በነገራችን ላይ፣ የወጣቶች የዕድገትና ልማት ፈንድ እንደሚዘጋጅ  በፕሬዚደንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ከተነገረ እና እቅዱ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ አራት ወራት ያህል አልፈዋል። የዚሁ አሁን ተዘጋጀ የተባለው ተዘዋዋሪ ፈንድ አስተዳደር ኃላፊነት ለገንዘብ እና ኤኮኖሚ ሚንስቴር፣ የንግድ ባንክ፣ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት እና የወጣቶች እና ስፖርት ሚንስቴር ተሰጥቷል። የዚሁ አዲስ እቅድ  አፈጻጸም ሂደት እንዴትነት እና በገሀድ የሚኖረው ትርጓሜ  ምን ይመስላል በሚል ውይይት አካሂደናል።

አርያም ተክሌ

ልደት አበበ