ተከሳሾቹ ተፈረደባቸዉ
ማክሰኞ፣ ጥር 7 2005ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአሸባሪነት የተወነጀሉ አስር ተከሳሾችን ከሰወስት እስከ ሃያ ዓመት በሚደርስ እስራትና በገንዘብ ቀጣ።የኦሮሞ ነፃ አዉጪ ግንባር (ኦነግ) አባላት ነበሩ የተባሉት እና ሐሰን ጃርሶ በተባሉት ኬንያዊ ተከሳሽ ይመሩ ነበር ከተባሉት አስራ-አንድ ተከሳሾች አንዱ ከዚሕ ቀደም በነፃ ተሰናብተዋል።ዛሬ አዲስ አባ ያስቻለዉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቅጣቱን ከወሰነባቸዉ ተከሳሾች መካካል ስድስቱ የተፈረደባቸዉ በሌሉበት ነዉ።የታሰሩት አራቱ ናቸዉ።ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ