ተቃውሞና ግጭት በባህር ዳር
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 13 2007ማስታወቂያ
የግጭቱ መንስዔ በባህር ዳር ከተማ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በበዓላት ቀናት የታቦታ ማደሪያ እንደሆነ የሚነገርለት መስቀል አደባባይ ለሌላ ሥራ ሊውል ነው በሚል መሆኑም ተዘግቧል።ጉዳዩን በቅርበት እንደተከታተሉ የገለፁልን እማኞች የግጭቱ መንስዔ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በተለያዩ የበዓላት ቀናት ለታቦት ማደሪያነት የምትጠቀምበት የመስቀል አደባባይ በመንገድ ማስፋፊያ የተነሳ ሊታረስ ነው በሚል መሆኑን ይናገራሉ።
በዓርብ ዕለቱ ግጭት በተቃውሞ ሰልፉ ያልተሳተፉ ሆኖም ከተማው ውስጥ የነበሩ ሌላ የባህር ዳር ነዋሪ በበኩላቸው ከግጭቱ በፊት እና በኋላ ስለተከሰተው የሚያውቁትን አብራርተዋል። በግጭቱ የሞቱ እና የቆሰሉ ሰዎች መኖራቸውን ተናግረዋል።
በግጭቱ የሞቱ ሰዎችን ቁጥር በውል ለማወቅ የባህር ዳር ከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አላዩ ጋር ደወልን። አገኘናቸው። ስብሰባ ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው መልሰን እንድንደውል ነገሩን። ሆኖም በገቡልን ቃል መሰረት በእጅ ስልካቸው ላይ በተደጋጋሚ ብንደውልም ስልኩ ሊነሳ አልቻለም። ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትንም ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ ከታች የሚገኘውን የድምፅ ማጫወቻ ይጫኑ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ