ተቃውሞና የወጣቶች ተሳትፎ በኢትዮጵያ
ዓርብ፣ ነሐሴ 6 2008ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የተቀሰቀሰው ተቃውሞ በማህበራዊ-ድረ ገጾች የሚደረጉ ውይይቶችን ተቆጣጥሯል። በአብዛኛው ወጣቶች የሚበዙበት የማህበራዊ ድረ-ገጾች ለወቅታዊው የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ከሌሎች የመገናኛ ብዙኋን ተመራጭ የሆኑ ይመስላል። በውይይቶቹ እና ክርክሮቹ የጸጥታ ኃይሎች በተቃዋሚዎች ላይ የወሰዱትን እርምጃ የሚያወግዙ አስተያየቶች ይበዛሉ። የዛኑ ያክል ተቃውሞዎቹን የሚያወግዙም አልጠፉም።
የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ሊቀመንበር ወጣት ነጂባ አክመል በተለያዩ አካባቢዎች በተቀሰቀሱ ተቃውሞቆች የተሳተፉ ወጣቶች ጥቂት ናቸው የሚል እምነት አላቸው።
ፀሃፊው፤የሰብዓዊ መብት አራማጁ እና ጦማሪው በፍቃዱ ኃይሉ አሁን የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታን ከሚከታተሉ አንዱ ነው።
በፍቃዱ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በሚታየው የአደባባይ ተቃውሞ የማህበራዊ ድረ-ገጾች ከፍ ያለ ሚና መጫወታቸውን ይናገራል።
እሸቴ በቀለ
ሒሩት መለሰ