ተቃዋሚ ፓርቲዎች መጠናከር ለምን ተሳናቸው ?
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 8 2004ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ ውስጥ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በይፋ መንቀሳቀስ ከጀመሩ የአንድ ወጣት እድሜ ቢያስቆጥሩም በአሁኑ ሰአት የአበብዛኛዎቹ እንቅስቃሴ መዳከሙ በግልፅ ይታያል ። ከተቃዋሚዎች በኩል ለዚህ በምክንያትነት የሚነሳው በገዥው ፓርቲ ኢህአዲግ የሚፈፀምባቸው ጫናና ወከባ ነው ። ይሁንና ከነርሱም በኩል ቢሆን ርስ በርስ ያለመግባባት ፣ለአንድ ዓላማ በህብረት ያለመቆምና የመሳሰሉት ድክመቶች እንዳሉባችወ በተደጋጋሚ ይወሳል ። ተቃዋሚዎች መጠናከር ያልቻሉባቸው ምክንያቶች እንዲሁም በኢትዮጵያ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት የሚያስችሏቸው ስልቶች የእንወያይ ዝግጅት ትኩረት ነው ። 3 እንግዶች የተካፈሉበት ውይይት እነሆ
ሂሩት መለሰ
ሸዋዮ ለገሰ