ቫቲካን እና የአዛውንቱ ኢትዮጵያዊ አርበኛ ጥያቄ
ረቡዕ፣ መስከረም 7 2007ማስታወቂያ
ማኅበር አባል የነበረችውን ብቸኛዋን አፍሪቃዊት ሀገር ኢትዮጵያን ከ79 ዓመት በፊት በወረረበት ጊዜ መሆኑን ነው የሚናገሩት። በዚሁ የኢጣልያ ወረራ ላይ ቫቲካን በከፊል ድርሻ እንዳላትም ምሁራኑ ይገልጻሉ። ፋሺስት ኢጣልያ በኢትዮጵያ ላይ ባካሄደው ወራራ ብዙ ሕዝቧ ማለቁ እና ከፍተኛ ጥፋት መድረሱ የሚታወቅ ነው። ኢጣልያ በዚያን ጊዜ ወረራ ለደረሰው ጥፋት ኢትዮጵያን እስከዛሬ ይቅርታ አልጠየቀችም፣ ካሳም አልከፈለችም። እና ይህን በተመለከተ አዛውንቱ ኢትዮጵያዊ አርበኛ ጀነራል ለማ ገብረማርያም ሰሞኑን ለቫቲካን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ግልጽ ደብዳቤ ልከዋል። ይህንኑ መነሻ በማድረግ ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ የአርበኞች ማኅበር ፕሬዚደንትን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
አርያም ተክሌ