ብክለትና ልማት18 የካቲት 2000ማክሰኞ፣ የካቲት 18 2000ልማት ሲታሰብ በብዙ ዘርፍ ቀድሞ የሚታየዉ ለአገር የሚያስገኘዉ የዉጪ ምንዛሪ፤ ለህብረተሰቡ የሚሰጠዉ ጥቅምና፤ የመሳሰሉት አዎንታዊ ጎኖች መሆኑ ግልፅ ነዉ።ለልማት እድገትና ለዉጪ ምንዛሪ ገቢ ሲታለም በሂደቱ ለተፈጥሮ ጥበቃ ትኩረት ቢሰጥ ከኋላ ፀፀት መዳን ይቻላል።https://p.dw.com/p/E0mb.........ከዛሬዉ ይታሰብበትምስል APማስታወቂያበተለያዩ ዘርፎች ለልማት በሚደረገዉ ርብርብ ስራ ላይ የሚዉሉ ተፈጥሯዊ ያልሆኑ የሂደቱ አጫፋሪዎች፤ ለምሳሌ በእርሻዉ ዘርፍ ብናይ ማዳበሪያና ተባይ ማጥፊያዉ ሁሉ የኋላ ኋላ አሉታዊ ጫናቸዉን በአካባቢ ላይ ጥለዉ ማለፋቸዉ አይቀርም።