1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ብንያም መሐመድ የከሰሳቸው የብሪታንያው የስለላ ድርጅት አባላትና ብይኑ፤

ዓርብ፣ ጥር 4 2004

መስከረም 1 ቀን 1994 ዓ ም፤ በኒውዮርክ ፣ መንትዮችን የዓለም የንግድ ማዕከላት ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎች አሸባሪዎች በማውደም የ 3 ሺ ያህል ህዝብ ህይወት እንዲቀጠፍ ካደረጉ በኋላ፤ ዩናይትድ እስቴትስ፤ በዓለም ዙሪያ የምትፈልጋቸውን አሸባሪዎች

https://p.dw.com/p/13jWr
የቀድሞው የሁዋንታናሞ እሥረኛ ፤ ብንያም መሐመድ፣ምስል AP

በኩባ  ደቡባዊው ምሥራቅ  ጫፍ ላይ በሚገኘው ሁዋንታናሞ ላይ በሚገኘው ምሽጓ፣ ልዩ እሥር ቤት በማዘጋጀት በዚያ ታጉር እንደነበረ የሚታወስ ነው። ተይዘው በዚያ እሥር ቤት ከተንገላቱት መካከል ፤ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ እንደተገለጸው፤ ከ 2 ዓመት ገደማ በፊት የተለቀቀው በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነው ብንያም መሀመድ ይገኝበታል። ብንያም፤ ለንግልትና የቁምስቅል እርምጃ በተባባሪነት  የብሪታንያ የስለላ ድርጅት አባላት ጎድተውናል ሲል ከሶ ነበር። የክሱን ውጤት አስመልክቶ ከለንደን ድል ነሣ ጌታነህ የሚከተለውን ዘገባ ልኮልናል።