1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ብሪታንያ በጥቃት ማግሥት

ሐሙስ፣ ግንቦት 17 2009

ማንቸስተር ብሪታንያ ዉስጥ ሰኞ ዕለት ከደረሰዉ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ጋር ግንኙነት አላቸዉ በሚል የተጠረጠሩ ስምንት ሰዎች መያዛቸዉ ተሰምቷል። ከተያዙት መካከል ጥቃቱን አድርሶ ከ22 ሰዎች በላይ ሕይወትን ያጠፋዉ ትዉልደ ሊቢያዊ ታላቅ ወንድም ይገኝበታል።

https://p.dw.com/p/2dZg8
Schweigeminute - Gedenken an die Opfer von Manchester
ምስል Reuters/D. Staples

M M T/ Beri. London (Manchester attack update) - MP3-Stereo

ጥቃት አድራሹ ራሱን እስላማዊ መንግሥት የሚለዉ ቡድን አባል መሆኑ መረጋገጡን ፖሊስ ጠቁሟል። የብሪታንያ ፖለቲከኞች ለደረሰዉ ጥቃት የፖሊስ በጀት እንዲጨመር ለቀረበዉ ጥያቄ በቶሎ ምላሽ አልሰጡም ያሏቸዉ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬዛ ሜይም ኃላፊነት አለባቸዉ እያሉ ነዉ። ለንደን በታጠቁ ወታደሮች መጠበቅ መጀመሯም ተነግሯል። ከለንደን ዘጋቢያችን ሃና ደምሴ ዘገባ ልካለች።

ሃና ደምሴ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ