1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሪታኒያ ምርጫ

ረቡዕ፣ ግንቦት 30 2009

ከአውሮጳ ኅብረት ለመውጣት በዝግጅት ላይ የምትገኘው እና በተከታታይ የሽብር ጥቃቶች የታመሰችው ብሪታኒያ በነገው ዕለት መሪዋን ትመርጣለች።

https://p.dw.com/p/2eHeO
Kombi-Bild Corbyn May TV-Debatte

Ber. London M M T/ Uk Election final campaign - MP3-Stereo

በጠቅላይ ሚኒስትሪቷ ቴሬሳ ሜይ የሚመራው ወግ አጥባቂ ፓርቲ እና በጄርሚ ኮብሪን የሚመራው የሊበር (የሰራተኞች) ፓርቲ ግንባር ቀደም ፉክክር ያደርጋሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ በማገባደጃ የምረጡኝ ቅስቀሳቸው  ብሪታኒያ ከአውሮጳ ኅብረት ለመውጣት የምታደርገውን ድርድር በብቃት መምራት የምችለው እኔ ብቻ ነኝ-ምረጡኝ ሲሉ ተደምጠዋል። የሊበር ፓርቲው ጄርሚ ኮብሪን ምርጫውን ካሸነፉ ለጤና እና የትምህርት አገልግሎት ከፍ ያለ ገንዘብ እንደሚመድቡ ቃል ገብተዋል። ቀደም ብለው የተሰበሰቡ የሕዝብ አስተያየቶች ግን በምርጫው አንድ የፖለቲካ ፓርቲ መንግሥት ለመመሥረት የሚያስችል ድምፅ ማግኘት መቻሉን የሚያጥራጥሩ ይመስላል።

ድልነሳው ጌታነሕ

እሸቴ በቀለ