1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቤጂ ካይድ ኢሴብሲ የቱኒዚያ ፕሬዚዳንት ሆኑ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 13 2007

ቱኒዝያ ዉስጥ በተካሄደዉ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተስፋ የተጣለባቸው አንጋፋ ፖለቲካኛ ቤጂ ካይድ ኢሴብሲ ማሸነፋቸዉ ተነገረ።

https://p.dw.com/p/1E8rK
Tunesien Präsidentschaftswahl 21.12.2014 - Beji Caid Essebsi
ምስል F. Belaid/AFP/Getty Images

ቤጂ ካይድ ኢሴብሲ 55,68 ከመቶ ድምፅ በማግኘት ነው ያሸነፉት። የ88 ዓመቱ ኢሴብሲ ፤ ተፎካካሪያቸው ሞንሴፍ ማርዙኪን በመለያ ምርጫው በከፍተኛ የድምጭ ብልጫ ማሸነፋቸውን የምርጫ ዘመቻው ቡድን አስቀድሞ ጠቁሞ ነበር። ስለሆነም ውጤቱ ይፋ ከመሆኑ አስቀድመው ነዉ ደጋፊዎቻቸዉ እና ራሳቸው ኢሴብሲም ደስታቸውን በይፋ የገለፁት።

«መጪው ህይወት ዛሬ ይጀምራል። አንድ እንሆናለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ሴቶች፣ ወንዶች ፣ ልጃ ገረዶች ሁላችሁም ለሰጣችሁኝ እምነት አመሰግናለሁ። »

ተፎካካሪያቸው ፤ የሀገሪቱ የሽግግር መንግስት ፕሬዚዳንት ሞንሴፍ ማርዙኪ ግን ወደቀድሞው አምባ ገነን ስርዕት ሀገሪቱ እንዳትመለስ በማስጠንቀቅ፤ ከዉጤቱ አስቀድመዉ ተፎካካሪያቸው አሸናፊነታቸዉን የሚያበስር ንግግር ማድረጋቸዉን ተችተዋል።

« የአሸናፊነት ገለፃው ዲሞክራሲያዊ አይደለም። ህግ እና ደንብን የምንከተል ሀገር መሆን ከፈለግን የምርጫውን ውጤት መጠበቅ ይኖርብናል።»

ዛሬ ከሰዓት በኋላ ይፋ በሆነው ውጤት መሠረት ማርዙኪ 44,32 ከመቶ በማግኘት ተሸንፈዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ደቡብ ቱኒዚያ ውስጥ በምትገኘው ሀማ ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች አንጋፋዉን ፖለቲከኛ ቤጂ ካይድ ኢሴብሲን በመቃወም ዛሬ አደባባይ ወጥተዋል። እንደ አካባቢው ነዋሪዎች ሰልፈኞቹ ጎማ በማንደድ ጎዳናዎችን ዘግተዋል። የፖሊስ ጣቢያ ዘልቀው ለመግባት የሞከሩ ሰልፈኞች ላይም የጥበቃ ኃይላት አስለቃሽ ጢስ መተኮሳቸው ተገልጿል።

አዜብ ታደሰ

ልደት አበበ