ባዶ እግሯሟ የሙዚቃ አምባሳደር
ረቡዕ፣ ጥር 23 2004ማስታወቂያ
የሙዚቃ ድግስዋን ስታሳይ በመድረክ ላይ የምትወጣዉ በባዶ እግሯ በመሆኑ ይታወቃል። ጫማ እንደማትወድ እና ገበያ ስትሄድ ሁሉ በባዶ እግሯ እንደሆነም ገልጻለች። ጤና ይስጥልኝ አድማጮች እንደምን ዋላችሁ የሲሳሪያ ኤቮራ ሙዚቃ እንደዚህ እንዳደመጣችሁት የምታዜምበት የፖርቱጋል ቋንቋ ፍችዉ ከቋንቋዉ ተናጋሪዎች ሌላ ባይገባም ዜማዉ ትዝታን ሃዘንን ፍቅርን ብቸኘትን ናፍቆትን እንዲህ እንዳደመጣችሁት ያሰንቃል ። ምዕራብ አፍሪቃዊትዋ የሙዚቃ ንግስት በመባል የምትታወቀዋ የካፕቬርዴዋ ሲሳሪያ ኤቮራ የአለምን የሙዚቃ መድረክ ለመጀመርያ ግዜ በሰማንያዎቹ አመተ ምህረት በአርባ ሰባተኛ አመትዋ ነዉ አሃዱ ብላ የተዋወቀችዉ። ወደዚሁ ግዙፍ መድረክ ከመቅረብዋ በፊት ግን ድህነት የአልኮል መጥጥ ችግር አንዱ ችግሯ እንደነበር ይነገርላታል። ያም ሆኖ በትዝታን መሰል ዜማዎችዋ በአገርዋ ያለዉን ችግረኛ ማህበረሰብ ተስፋ በመስጠት እና በቻለችዉ ሁሉ ችግረኛን በመርዳትዋ ትታወቃለች። ስለ ከያኒዋ ሰፋ ያለ ዘገባ ይዘናል! ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ!
አዜብ ታደሰ
ሸዋዪ ለገሰ