1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ባራክ ኦባማ በአውሮፓ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 1 2001

በየሄዱበት ፍቅርና አድናቆት የሚቸራቸው የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በአንድ ሳምንቱ የአውሮፓ ጉብኝታቸው ተመሳሳዩ ከበሬታ እና አድናቆት አልተለያቸውም ።

https://p.dw.com/p/HU4h
ባራክ ኦባማምስል AP

የአውሮፓን ምድር እንደረገጡ ለማዳመጥና ለመመካከር ነው የመጣሁት ማለታቸውና ይህንኑም ቃላቸውን ጠብቀው መገኘታቸው ከለንደን እስከ ፕራግና ኢስታንቡል ድረስ የሞቀ አቀባበል አትርፎላቸዋል ።አውሮፓውያን ለኦባማ የሰጡት ክብር ከርሳቸው ለቀደሙት ጆርጅ ቡሽ ይሰጡ ከነበረው የላቀ ሆኖ ተገኝቷል ። በሉቨን ዩኒቨርስቲ የፓለቲካ ሳይንስ ምሁር ፕሮፌሰር ኬርማን ባርት እንደሚሉት አውሮፓውያን ይህን ያደረጉበት ምክንያት አላቸው ።

ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሀመድ