1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ባለዲግሪው ጋዜጣ ሻጭ በኢትዮጵያ

ዓርብ፣ መጋቢት 28 2004

በኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞች መብት ምን ያህል ይከበራል፣ ተግባራዊ ጥበቃውስ ምን ይመስላል? የዛሬው የወጣቶች ዓለም መሰናዶ ርዕስ ነው። የ24 ዓመቱ ወጣት ግዛቸው አዘዘው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፍልስፍና ትምህርት በዲግሪ መርሐ-ግብር እንደተመረቀ ገልጿል።።

https://p.dw.com/p/14Z53
የአካል ጉዳተኞች መብት
የአካል ጉዳተኞች መብትምስል DW

በኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞች መብት ምን ያህል ይከበራል፣ ተግባራዊ ጥበቃውስ ምን ይመስላል? የዛሬው የወጣቶች ዓለም መሰናዶ ርዕስ ነው። የ24 ዓመቱ ወጣት ግዛቸው አዘዘው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፍልስፍና ትምህርት በዲግሪ መርሐ-ግብር እንደተመረቀ ገልጿል።ይሁንና ግን ወጣቱ በአካል ጉዳተኝነቴ የተነሳ ብቻ እስካሁን ስራ ለማግኘት አልቻልኩም ሲል ምሬቱን  አሰምቷል። ጉዳዩ የሚመለከታቸው የሰራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስትር መስሪያ ቤት ባለሙያዎችን አነጋግረናል። የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ብሔራዊ ማኅበር ፕሬዚደንትም መልስ አላቸው።

በኢትዮጵያ ቁጥራቸው ትንሽ የማይባል የአካል ጉዳተኞች ከማህበረሰቡ ከሚደርስባቸው የተለያዩ ጫናዎች ባሻገር በጥረታቸው ከፍተኛ ደረጃ ሲደርሱ ይስተዋላል። በዛው መጠን ደግሞ ምንም ያህል ጥረት ብናደርግም መብታችን በተገቢው መንገድ አልተጠበቀልንም የሚሉ አይታጡም። ከቅሬታ አቅራቢዎቹ መካከል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዲግሪ እንደተመረቀ የገለፀልን የ24 ዓመቱ ወጣት ግዛቸው አንዱ ነው።

ማንተጋፍቶት ስለሺ 

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ