1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ባህል ነክ ክስተቶች በጀርመን

ሐሙስ፣ ጥር 5 2003

የአዉሮጻዉያኑ 2011 አ.ም ከጀመርን ሳምንታት ተቆጠሩ፣ የጎርጎረሳዉያኑ አዲስ አመት ከገባ በጀርመን የባህል ድረ-ገጾች ምን አበይት ነገሮችን አስፍረዋል?

https://p.dw.com/p/Qrlc
ታሊንምስል picture-alliance/ZB

የአዉሮጻዉ ህብረት እዝያ ራቅ ብሎ በሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ በአዉሮጻዉያኑ 2011 አ.ም ከባህር የሚፈሰዉን ታሪክ ማስደመጥ ይፈልጋል ይላል በዚህ በአዉሮጻ በተለያዩ የባህል ድረ-ገጾች የአመቱ መጀመርያ ሆኖ የቀረበዉ ርዕስ። ዘንድሮ ታሊን የኢስቶንያ ዋና ርዕስ ከተማ ብቻ ሳትሆን የአዉሮጻዉያኑ 2011 አ.ም የባህል ማዕከል ሆና መመረጥዋንም ለማብሰር። በቀድሞዋ የሶቭየት ህብረት የባልቲክ ግዛቶች አንድዋ የሆነችዉ ኢስቶንያ ዋና ከተማ ታሊን ፊላንድን በሚያዋስነዉ የባልቲክ ባህርን ተንተርሳ በተለይ ለአዉሮጻዉያኑ እድምተኞች በሙዚቃ በትያትር እንዲሁም ቤተ መዘክር አሰባሰባ የያዘችዉን የዘመናት ባህልና ታሪክ ለአለም እንድታሳይ ተመርጣለች። አራት መቶ ሺ ነዋሪዎችን የያዘችዉ የባልቲክ ባህር የወደብ ከተማ ታሊን ከባህር የሚቀዳዉን ታሪክ እንደምስታደምጥም ነዉ የተነገረላት። የታሊኑ የባህል ማዕከል ቃል አቀባይ ወሮ ማሪስ ሄልራንድ ታሊን ከባህር የሚቀዳዉን ታሪክ ሲባል ይላሉ

«የከተማዋ ታሪክ ከባህሩ ጋር የተያያዘ ነዉ፣ ህዝብም ቢሆን የታሊንን ከተማ ታሪክ ከባህሩ ጋር በማያያዝ ነዉ የሚገልጸዉ» ማሪስ ሄልራንድ በቀድሞዋ የሶብየት ህብረት ዘመን የልጅነታቸዉን ግዜ ያስታዉሳሉ። ኢስቶንያ በሶቭየት ህብረት ስር በነበረችበት ወቅት ታሊን ከተማ የሚያዋስነዉ የባልቲክ ባህር ለወታደራዊ እንቅስቃሴ ብቻ የታገደ ቦታ በመሆኑ ሲቪሉ ህዝብ ባህሩን አቋርጦ ወደ ከተማዋ መዝለቅ የተከለከለ ነበር። ኢስቶንያ ነጻነትዋን ከያዘችም በኳላ በቦታዉ የወታደር እንቅስቃሴ ባይኖርም ቅሉ ገና ቦታዉ መገናኛ እየተበጀለት ነዉ።

«በአስራ ዘጠነኛዉ ክፍለ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሪ አምስት አመት ድረስ ያገለገለ እስር ቤት ታሪካዊ ህንጻ ታሊን ከተማ ወደብ ላይ ይገኛል። ይህ እስር ቤት በመታደስ ላይ ነዉ፣ ባህሩን ከከተማዋ የሚያገኛኝ መሃከል ቦታ ስለሆነም የስነ-ጥበብ መንገድ ብለን የከተማዋን የተለያዩ ባህል ነክ ነገሮችን አምጥተን ህዝብን ቦታዉ ላይ እንዲገኝ ማድረግ እንሻለን» በያዝነዉ የአዉሮጻዉያኑ 2011 አ.ም ኢስቶንያ እራስዋን ዘመናዊ አድርጋ ለቀሪዉ የአዉሮጻ አገራት ማሳየትን ትሻለች። በዚህም አንዱ ከዛሪ አስራ ሶስት ቀን በፊት ጀምሮ የአዉሮጻ መገበያያ ገንዘብ ይሮን ተጠቃሚ በመሆን አስራ ሰባተኛዋ የአዉሮጻዉ ህብረት አገር ሆናለች። የወደብ ከተማ ታሊን ከሃምሳ አንድ አመት በኳላ እንደ አ.አ 1991 አ.ም በኳላ ኢስቲንያ ከሶቭት ህብረት ነጻ ስትወጣ ነበር፣ ዳግም በዋና ከተማነት የተመረጠችዉ። የታሊን ጥንታዊዉ ማዕከላዊ ከተማ በሰሜናዊ አዉሮጻ የመካከለኛዉን የሰዉ ልጅ የኑሮ ዘመን የሚገልጽ በእደናቂ ሁኔታ ተጠብቆ የቆየ ታሪክ ማስረጃ በመገኘቱም በተባበሩት መንግስታት የትምህርት እና ባህል ድርጅት ማለት በዪኒስኮ የአለም የባህል ቅርጽነት ተመዝግቦአል። በምስራቅ ባህር ላይ የተመሰረተችዉ የባልቲክ ከተማ ታሊን ሰሜናዊ ጀርመን ከተማ ሮስቶክን ፊላንድ ከተማ ሄልሲንኪን እና የሩስያዋን ሳንት ፒተርስበርግ ከተማን በማገናኘት በቁልፍ ከተማነትዋም ትታወቃለች። ዘንድሮ የአዉሮጻዉ ሸንጎ ለኢስቶንያዋ ታሊን ከተማ ባሻገር በፊላንድ ጥንታዊ ከተማነትዋ የምትታወቀዉ እና ፊላንድ ደቡብ ምዕራብ ላይ የምትገኘዉን ቱርኩ ደሴት ከተማ በባህል ማዕከልነት መርጦአል። የፊላንድዋ ቱርኩ ደሴት ከተማ ዘንድሮ አመትዋን መያዝዋ ተዘግቦላታል። 175,000 ነዋሪዎችን የያዘችዉ የፊላንድ ቱርኩ ከተማ በመካከለኛዉ ክፍለ ዘመን የተገነቡ እጅግ ጥንታዊ ቤቶች የሚገኙባት መሆንዋም ተነግሮአል።

Merkez Moschee in Duisburg
በዲስኑርግ ከተማ የሚገኝ መስጊድምስል AP

ሌላዉ በጀርመኑ የባህል ድረ-ገጽ ላይ ሰፍሮ የሚገኘዉ ሰፊ ርዕስ እስልምና ለጀርመን ሃይማኖት አንዱ አካል ነዉን የሚለዉ ጥያቄ ነዉ። በጀርመን ወደ አራት ሚሊዮን የሚሆኑ ሙስሊሞች ይኖራሉ። ስለ ሙስሊም ብዙ ነገር ቢጻፍና ቢነገርም በጀርመን ስለ እስልምና በቂ እዉቀት ባለመኖሩ አልያም ትክክለኛ ሃሳብ ባለመሰጠቱ አሁንም ቢሆን በርካታ ጀርመናዉያን የሙስሊም ማህበረሰቦችን በግልጽ አያቋቸዉም። ይህንን ችግር ለመፍታትና የእስልምና ሃይማኖትን ለህዝብ በግልጽ ለማሳየት የጀርመን የባህል ማዕከል ሰፊ ጥያቄን እና ትንተናን ያዘለ የጥናት ጽሁፍ አዘጋጅቶአል። ይኸዉም የእስልምና ሃይማኖት ባህል በጀርመን፣ የእስልምና ሃይማኖት አባት ለመሆን በጀርመን የሚሰጥ ሃይማኖታዊ ትምህርት፣ የሌላ አገር ዝርያ ያላቸዉ የጀርመን የብዙሃን መገናኛ ሰራተኞች፣ እንዲሁም እስልምና ሃይማኖት በወቅታዊዉ የጀርመን ፖለቲካ ዉስጥ ስላለዉ ሚና ያነሳል። ይህን ሰፊ መዘርዝር ያዘለ መጠይቅ እና ማብራርያ ሃምሳ ያህል ጸሃፊዎች የተሳተፉበት ሲሆን ጸሃፍቱ ተሰባስበዉ ሰፊ ጥያቄዎችን እና መልሶችን ጥናታዊ ጽሁፎችን እንዲያቀርቡ ለማሰባሰብ ምንም ችግር እንዳልገጠማቸዉ የጀርመኑ የባህል ማእከል ዋና ተጠሪ ኦላፍ ዚመር ማን ይገልጻሉ። «ይህንን ሰፊ ትንተና እና ጥያቄ ያዘለ ጽሁፍ ካቀረቡት መካከል ስለ እስልምና ሃይማኖት ጥናት የሚያደርጉ እራሳቸዉ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ የሆኑ ይገኙበታል። በሌላ በኩል በዚሁ ጽሁፍ ላይ ለምሳሌ የጀርመን ህገ መንግስት ጥበቃ ቢሮ ፕሪዝደንትም ተካፍለዉበታል። እዚህ ላይ ዋናዉ ጥናታችን ትክክለኛ ሃሳብን በማስቀመጥ ጽሁፉ የተሟላ ገጽታ እንዲኖረዉ ነዉ የምፈለግነዉ»

Flash - Galerie Orchideenfächer in Deutschland Singen mit Kindern
Ein Kinderchor singt in der Stadtkirche in Freudenstadt, aufgenommen am Freitag (17.04.2009). Foto: Patrick Seeger dpa/lsw +++(c) dpa - Report+++ምስል DW

ለማወቅ ነገርን መተንተን እና መረዳት አስፈልጓል ይላሉ በጀርመን የሙስሊም ምክር ቤት ተጠሪ አይማን ማዝያክ። በጀርመን ስለሙስሊም የሚሰጠዉ ገጽታ በኒዮርክ ከደረሰዉ ከፍተኛ የአሸባሪዎች ጥቃት ወዲህ ሊለወጥ አለመቻሉ፣ በጀርመን የደረሱ አንዳንድ ጥቃቶች እና ችግሮች፣ ሌላዉ በቅርቡ አንድ የሶሻል ዲሞክራቶች ፓርቲ አባል በጀርመን ሙስሊምን በመንቀፍ ያወጡት ጽሁፋቸዉ ህዝቡ ስለ ሙስሊም ያለዉን እዉቀት እንዳያሰፋ አግዶታል። በዚህም የተማረዉም ሆነዉ ጥቂት እዉቀት ያለዉ ባለሃብቱም ሆነ ሃብት የሌለዉ አብዛኛዉ ዜጋ ሙስሊሞች ላይ ያለዉ አመለካከት ሚዛናዊ ያልሆነ ነዉ። ባለፈዉ የአዉሮጻዉያኑ አመት ጀርመን የተዋሃደችበትን ሃያ ኛ አመት ስታከብር የጀርመኑ ርእሰ ብሄር ክርስትያን ዎልፍ እስልምና የጀርመን አንዱ አካል መሆኑን መናገራቸዉ በፓርቲያቸዉ በክርስትያን ዲሞክራቶች ብቻ አልነበርም ቁጣን ያስነሳባቸዉ። አራት ሚሊዮን ሙስሊሞች በጀርመን ይኖራሉ። ጀርመናዉያን በመሆናቸዉም የጀርመን አንድ አካልነታቸዉ ሙሉ ተቀባይነት ያለዉ ጉዳይ ነዉ። ግን እዚህ ላይ አሁንም እስልምና የጀርመን አንዱ አካል ነዉ የሚለዉን ሃሳብ መቀበል አለመቻል የብዙሃኑ ጀርመናዉያን እምነት ነዉ። በጀርመን ተዋህዶ ለመኖር ቋንቋን ባህልን ማወቅ ተገቢነቱ ብዙ ግዜ የሚነሳ ነጥብ ሆኖ ሳለ እስካሁን ሃይማኖትን ለማወቅ የሚነሳ ጥያቄ ሲጎተት አልያም በጥልቅ መፍትሄ ሳያገኝ ተድበስብሶ የሚያልፍ ጉዳይ ሆኖ ይገኛል። በጀርመን ከአስራ ስድስት አመት እድሜ በታች የሆኑ የሌላ አገር ዜጋ ልጆች ስድሳ በመቶዉ ሙስሊሞች ናቸዉ። በዚህም ነዉ የነገዋን ጀርመን ለመገንባት ዛሪ የጀርመን የባህል ማዕከል ቢሮ እስልምና የጀርመን አንዱ አካል ነዉን በሚል የተለያዩ ጽሁፎችን በማቅረብ ዉይይትን የጀመረዉ።

ሙዚቃ የመንፈስ ምግብ ስንቅ ናት በሙዚቃ እዉነት እና ዉበት ፍቅር ይገለጻል። በሙዚቃ ጀግና ይወደሳል የአገር ፍቅር ናፍቆት ብቻ ሳይሆን በሙዚቃ ሃዘንም ይገለጻል። ታድያ ሙዚቃ በሰዉ ልጅ ህይወት ዉስጥ ሁሉንም ናት። በጀርመን ወደ ሰባት ሚሊዮን ያህል ህዝብ የእረፍት ግዜዉን ሙዚቃ በማዳመጥ አልያም በማዜም እንደሚያሳልፍ ተገልጾአል። ሙዚቃ ስንል የፖፕ ሙዚቃ ሆነ ሪጌዉን አልያም በቤተ ክርስትያን የሚዜመዉን የህብረት ሙዚቃ አልያም ጃዝ ሁሉ ያጠቃልል። በዚህም ይላሉ ጀርመናዉያን ጠበብቶች ሙዚቃ የትኛዉም አይነት መልኩ ህዝብን ከህዝብ የሚያገናኝ ታላቅ ድልድይ ነዉ። በጀርመን በአመት ዉስጥ ስድሳ ሚሊዮን የሚጎበኘዉ ሶስት መቶ ሽ ያህል ከፍተኛ የሙዚቃ ድግስ ይካሄዳል። ማዜም የሰዉ ልጅ ያለዉን የማስተዋል መጠን ያዳብራል በተለይ ለህጻናት ሙዚቃ ወይም ዜማ ትምህርታቸዉን አጤነዉ እንዲይዙ ቋንቋ ችሎታቸዉን እንዲያዳብሩ ይረዳል። እዚህ በኖርዝ ራይን ዊስት ፋልያ ግዛት በቩፐርታል ከተማ ባለ መዋለ ህጻናት ልጆች በሙዚቃ ቋንቋን ሲማሩ እናደምጣለን። በጽናፋዊዉ ትስስር ማለት በግሎባላይዜሽኑ አለም ቋንቋ ቀዳሚዉን ስፍራ ይዞአል። በተለይ በአዉሮጻዉ ህብረት አገራት የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ከአፍ መፍቻ ቋንቋቸዉ በተጨማሪ ሌላ ሁለት ቋንቋን መማር የግድ ነዉ። ለምሳሌ በቩፐርታል ህጻናት መዋያ ያሉ ህጻናት ቤተሰቦቻቸዉ ከአልጀርያ ከቱርክ ከስፔን አልያም ከጀርመን እና ከጣልያን የመጡ ናቸዉ። ከአፍ መችቻ ቋንቋቸዉ ሌላ በሚዉሉበት በህጻናት መዋያ ከጠባቂዎቻቸዉ ጋር በጀርመንኛ ቋንቋ ይግባባሉ። በጎን ፈረንሳኛ ቋንቋን በሙዚቃ ይማራሉ። በጀርመን ባሉ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ዉስጥ የሚሰጠዉ የሙዚቃ ትምህርት ኖታ ህጋዊነቱ ለጀርመን ትምህርት ቤቶች ሁሉ ተወስኖ ተማሪዎች ያለምንም እክል የሙዚቃ ኖታን በመገልበጥ ትምህርታቸዉን ይማራሉ። ይህን የሙዚቃ ኖታን እንደልብ የመገልበጥ ህግ ከትምህርት ቤቶች ባለፈ መዋለ ህጻናትን አይጠቅስም። ይኸዉም በጀርመን በአንድ የህጻናት መዋያ ህጻናትን የምትጠብቅ የህጻናቱ አስተማሪ ለተማሪዎችዋ የሙዚቃ ኖታን ገልብጣ ለተማሪዎችዋ በመስጠትዋ የምታስተምርበት የህጻናት መዋያ ተከሶ ወደ ሁለት መቶ ይሮ የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍል ተወስኖበታል። በዚህም በጀርመን በህጻናት መዋያ ያለዉን መዝሙርም ሆነ ሙዚቃን ለመጠቀም ህግ ባለመዉጣቱ ህጻናትን በህጻናት መዋያ ሙዚቃን እንደልባቸዉ እንዳይማሩ ያደረገ ድንቃፍ ነዉ በሚል ቅሪታን መቀስቀሱ የጀርመን የባህል ድረ-ገጽ ትኩረቱን እንዲጥል ጋብዞታል። ቀሪዉን ቅንብር ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ