ባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 14 2001ማስታወቂያ
ባለፈው ሳምንት፤ ጀርመን አገር፣ ሀምቡርግ ከተማ ውስጥ ስለሚገኘውና “የፈረስ ጋጣ ባህል ማዕከል” ስለሚባለው አንድ የባህል ማዕከል ማንሳታችን ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ የአገሪቱን ባህልና ጥበብ ከማበልፀግ አንፃር ምን ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ የሚለው ነጥብ ላይ እናተኩራለን። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከልም ማንጸሪያችን ይሆናል። ቀድሞ በዚህ የባህል ማዕከል ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ የጥበብ ሰዎች መካከል አንዱ የሆነው አርቲስት ሸዋፈራሁ ደሳለኝና አርቲስት ገረመው አሰፋ የሚሉን ይኖራቸዋል።