1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ባህላዊ የበአል አከባበር እና ወጣቱ

እሑድ፣ ጥር 30 2002

ከዝያዉ ማርልኝ ያን ገበሪ፣ ከዝያዉ ማርልኝ ያን ገበሪ፣ ይዤዉ እንዳልመጣ ይጠብቃል በሪ! ብላ ገጠመች አሉ አንዲት የገበሪ ሚስት ባልዋ ስራ በዝቶበት ጥምቀት በአል ላይ ባለመገኘቱ፣

https://p.dw.com/p/Lufc
ላሊበላምስል picture-alliance / Bildagentur Huber
ጤና ይስጥልኝ አድማጮች እንደምን ዋላችሁ፣ የዛሪ ሁለት ሳምንት ግድም በአገራችን የጥምቀት በአል አከባበር በማስመልከት ባህላዊዉን ሃይማኖታዊዉን ወግ ይዘን በጥቂቱ ዳሰን፣ የሎሚ ዉርወራዉን ወጉን የሚያካፍለን አድማጭ ካለ ብለን በጠየቅነዉ መሰረት ከአድማጮች መልሰ አግኝተናል። ነጭ ዶሮ ቀይ ዶሮ ይላል ዛር አንጋሽ፣ አይኗ ሰዉ ይገላል ከንፈሯ ሲሸሽ፣ ሲል ወንዱ ያሞግሳል በባእላት ላይ ወጣት ወንድ ሴትዋን፣ ሴትዋም በበኩሏ ወንዱን እንዲህ በማለት ታሞግሳለች፣ በአይን የወደችዉን ፍቅሯን ትገልጻለች። አይኑ የሚመስለዉ የተሶረፈ አዉሪ (የተቆጣ አዉሪ)፣ ባቱ የሚመስለዉ የፈረንጅ ገባሌ፣ አንገቱ የሚመስለዉ ጠጅ የወረደበት፣ ጸጉሩ የሚመስለዉ ንብ የሰፈረበት፣ ደረቱ ሚመስለዉ የትዩን ሰገነት፣ ከሱ ጋር ያደረ ምን ኩነኔ አለበት! ሌሎች አባቶቻችን ስሜታቸዉን ፍቅራቸዉን የሚገልጹበት ዉበት ያላቸዉ ስነ-ግጥሞቻችን አሰባስበን ይዘናል ያድምጡ!
አዜብ ታደሰ