ባህላዊ ህክምና በኢትዮጵያ
ረቡዕ፣ መጋቢት 25 2005ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ ውስጥ ከዘመናዊ መድኃኒት በበለጠ በስፋት ጥቅም ላይ የሚውለው የባህል መድሐኒት በጥናትና ምርምር ሊደገፍ እንደሚገባ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሞያዎች አሳሰቡ ። የባህል መድሐኒት አዋቂዎች ተመራማሪዎች እንዲሁም የጤና ባለሞያዎች አዲስ አበባ ውስጥ ባካሄዱት አውደ ጥናት እንደተነገረው ባህላዊውን ህክምናን ከዘመናዊ ህክምና ጋር ማቀናጀቱ አሁንም አወዛጋቢ ሆኖ እንደቀጠለ ነው ። የኢትዮጵያ ባህላዊ መድሓኒት አዋቂዎች ማህበር ፣በአሁኑ ጊዜ ትክክለኛውንና ሃሰተኛውን የባህል መድኃኒት አዋቂ መለየቱ ደግሞ ሌላው አሰቸጋሪ ጉዳይ መሆኑም አስታውቋል ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ አለው ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ