ቢቢሲ ባንድ ኤይድን ይቅርታ መጠየቁ25 ጥቅምት 2003ሐሙስ፣ ጥቅምት 25 2003ባንድ ኤይድ የተባለው የዕርዳታ ድርጅት ለ 1977 ቱ የኢትዮጵያ ረሀብ መርጃ ያሰባሰበው በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ለጦር መሣሪያ መግዣ ውሏል ሲል የብሪታኒያ ዜና መሰራጫ ኮርፖሬሽን ቢቢሲ ባለፈው ዓመት ላሰራጨው ዘገባ ዛሬ ይቅርታ ጠየቀ ።https://p.dw.com/p/PyXMቦብ ጌልዶፍምስል APማስታወቂያቢቢሲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በዘገባው ምክንያት ስለ ድርጅቱ የተሳሳተ ግንዛቤ በመፈጠሩ ጥፋተኛ መሆኑን አስታውቋል ። የህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ የቀድሞው ከፍተኛ የአመራር አባልና በወቅቱ የድርጅቱ ወታደራዊ ክፍል ሀላፊ የነበሩት ዶክተር አረጋዊ በርሄ የቢቢሲ ይቅርታ አስገራሚ ነው ይላሉ ። ሂሩት መለሰ ነጋሽ መሐመድ