ቡርቃና ጀርመናውያን
ማክሰኞ፣ ግንቦት 10 2002ማስታወቂያ
ይህ በቤልጂግ ተጀምሮ በፈረንሳይ የቀጠለው በቡርቃ ላይ የተወሰደ ጥብቅ ዕርምጃ በሌሎች የአውሮፓ ሐገራትም ተግባራዊ ሊሆን እንደሚችል የብዙዎች ግምት ነው ። ጉዳዩ እዚህ ጀርመንም በየምክንያቱም ማነጋገሩ አልቀረም ። የቡርቃ መታገድ ደጋፊዎች አለባበሱ ከባህላዊ እሴቶቻችን ውጭ ከመሆኑም በላይ የሴቶች ጭቆና ምልክት ነው በማለት ሴቶች ፊታቸውን ሸፍነው እንዲሄዱ መፈቀድ የለበትም ይላሉ ። በሌላ ወገን ደግሞ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እናራምዳለን በሚሉ ሐገራት የሰዎች አለባበስ ላይ ገደብ መጣሉ ተገቢ አይደለም ፤ እገዳው የአለባበስ ነፃነትን ይጋፋል ሲሉ የሚከራከሩም አሉ ። ክርክሩ በዚህ መልኩ በቀጠለበት ሁኔታ ጀርመናውያን ስለ ቡርቃ ምን አስተያየት እንዳላቸው ለመረዳት የዶይቼቬለ ራድዮ የአረብኛ ቋንቋ ክፍል ባልደረባ ሻምስ አያሪሽ ቡርቃ ለብሳ በኮሎኝ ከተማ ተዘዋውራ ነበር ። በዛሬው ዝግጅታችን ልምድዋን ታካፍለናለች ።
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ