1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቡሩንዲና የዐባይ ወንዝ ተፋሰስ አገሮች ማኅበር፣

ሐሙስ፣ የካቲት 24 2003

የዐባይ ወንዝ ተፋሰስ አገሮች የውሃ አጠቃቀም አዲስ ውል ፣ ባለፈው ዓመት በግንቦት ወር አዲስ አበባ ውስጥ ሲፈረም፣ በዚያ ወቅት፤

https://p.dw.com/p/R64x
ምስል AP

በምርጫ ሳቢያ እንደማያመቻት ገልጻ  በሥነ ሥርዓቱ ያልተገኘችው ቡሩንዲ ፤ ከትናንት በስቲያ  ይጠበቅ የነበረውን የውዴታ ግዴታውን እውን አድርጋለች። ይህ የአሁኑ የቡሩንዲ እርምጃ በአባል ሃገራቱ ዘንድ የሚኖረው ትርጓሜ ምን ይሆን? ---ተክሌ የኋላ----

ቡሩንዲ፣ የዐባይ ወንዝ ተፋሰስ አገሮችን የውሃ አጠቃቀም ውል ከትናንት በስቲያ በመፈረም፣ ከኬንያ፤ ዩጋንዳ፣ ታንዛንያ፣ ኢትዮጵያና ሩዋንዳ ቀጥላ 6ኛዋ  ሀገር ሆናለች። ይህ ፤ አሁን፣ ለአባል ሀገራቱ ምን ዓይነት ትርጓሜ ይኖረው ይሆን!ውሉስ መቼ ይሆን ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው? ዋና ጽ/ቤቱ፤  በኢንተቤ፤ ዩጋንዳ የሚገኘው የዐባይ ወንዝ ተፋሰስ አገሮች ማኅበር ቃል አቀባይ ምስተር ዳንኤል ሜቦያ---

«ውሉ፣ ከሞላ ጎደል በ 6 አገሮችተፈርሟል። ውሉ፤  ለእያንዳንዱ ፓርላማ ቀርቦ መጽደቅ ያለበት ሲሆን ፣ ትንሽ ጊዜ ሊወስድ ይችላል። ከእንግዲህ እንዲጸድቅ የሚደረግበት ሂደት ነው የሚከተለው። ጊዜ ሊወስድ ይችላል፤ ምን ያህል ጊዜ? በትክክል ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል የሚያውቅ የለም።»

ቡሩንዲ፤ ዘግየት ብላም ቢሆን አሁን መፈረሟ፣ በዐባይ ተፋሰስ አገሮች ማኅበር ዘንድ፣ በአንገራጋሪዎቹ፣ ግብፅና ሱዳንም በኩል እንዴት ይታይ ይሆን? በኢትዮጵያ የውሃና የኃይል ምንጭ(ኢነርጂ) ሚንስቴር የወሰንና የወሰን ተሻጋሪ ወንዞች ጉዳይ አመራር(ዳይሬክተሬት) ዋና ሥራ መሪ(ዳይሬክተር) አቶ ተፈራ በየነ--

(ድምፅ)----

የዐባይ ተፋሰስ አገሮች የሚንስትሮች ም/ቤት ልዩ ስብሰባ በቅርቡ የሚካሄድ መሆኑን የገለጡት ዳንኤል ሜቦያ፣ የአንገራጋሪዎቹ አገሮች አቋም ፣ አሁን አዲስ የሽግግር አስተዳደር የመሰረተችው ግብፅ ጭምር ሊታወቅ እንደሚችል ጠቁመዋል። ከ 6 ወር ገደማ በኋላ፣ ነጻነት ታውጃለች  ተብላ የምትጠበቀው ደቡብ ሱዳን ምን አቋም እንደሚኖራት የሰጠችው ፍንጭ ይኖር ይሆን?--አሁንም ዳንኤል ሜቦያ---

«እስካሁን ምንም ዓይነት ምልክትም ሆነ ፍንጭ አላገኘንም። ስለደቡብ ሱዳን ለጊዜው ብዙም የምንለው የለም። እስከ ሐምሌ ፤ አገሪቱ ሙሉ-በሙሉ ነጻ መሆኗን እስክታውጅ ጠብቀን መመልከቱ ሳይሻል አይቀርም። ለጊዜው የዐባይን ተፋሰስ አገሮች ማኅበር እንቅሥቃሤ በተመለከተ ከደቡብ ሱዳን ዜናም  ሆነ መረጃ የለንም። ስለዚህ መጠበቅ ይኖርብናል።»

ቡሩንዲ  ውል በመፈረሟ፤ ለኢትዮጵያ ያለው ጠቀሜታ እንዴት ይገመገማል? 

(ድም

ቡሩንዲና የዐባይ ወንዝ ተፋሰስ አገሮች ማኅበር፣

የዐባይ ወንዝ ተፋሰስ አገሮች የውሃ አጠቃቀም አዲስ ውል ፣ ባለፈው ዓመት በግንቦት ወር አዲስ አበባ ውስጥ ሲፈረም፣ በዚያ ወቅት፤ በምርጫ ሳቢያ እንደማያመቻት ገልጻ  በሥነ ሥርዓቱ ያልተገኘችው ቡሩንዲ ፤ ከትናንት በስቲያ  ይጠበቅ የነበረውን የውዴታ ግዴታውን እውን አድርጋለች። ይህ የአሁኑ የቡሩንዲ እርምጃ በአባል ሃገራቱ ዘንድ የሚኖረው ትርጓሜ ምን ይሆን? ---ተክሌ የኋላ----

ቡሩንዲ፣ የዐባይ ወንዝ ተፋሰስ አገሮችን የውሃ አጠቃቀም ውል ከትናንት በስቲያ በመፈረም፣ ከኬንያ፤ ዩጋንዳ፣ ታንዛንያ፣ ኢትዮጵያና ሩዋንዳ ቀጥላ 6ኛዋ  ሀገር ሆናለች። ይህ ፤ አሁን፣ ለአባል ሀገራቱ ምን ዓይነት ትርጓሜ ይኖረው ይሆን!ውሉስ መቼ ይሆን ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው? ዋና ጽ/ቤቱ፤  በኢንተቤ፤ ዩጋንዳ የሚገኘው የዐባይ ወንዝ ተፋሰስ አገሮች ማኅበር ቃል አቀባይ ምስተር ዳንኤል ሜቦያ---

«ውሉ፣ ከሞላ ጎደል በ 6 አገሮችተፈርሟል። ውሉ፤  ለእያንዳንዱ ፓርላማ ቀርቦ መጽደቅ ያለበት ሲሆን ፣ ትንሽ ጊዜ ሊወስድ ይችላል። ከእንግዲህ እንዲጸድቅ የሚደረግበት ሂደት ነው የሚከተለው። ጊዜ ሊወስድ ይችላል፤ ምን ያህል ጊዜ? በትክክል ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል የሚያውቅ የለም።»

ቡሩንዲ፤ ዘግየት ብላም ቢሆን አሁን መፈረሟ፣ በዐባይ ተፋሰስ አገሮች ማኅበር ዘንድ፣ በአንገራጋሪዎቹ፣ ግብፅና ሱዳንም በኩል እንዴት ይታይ ይሆን? በኢትዮጵያ የውሃና የኃይል ምንጭ(ኢነርጂ) ሚንስቴር የወሰንና የወሰን ተሻጋሪ ወንዞች ጉዳይ አመራር(ዳይሬክተሬት) ዋና ሥራ መሪ(ዳይሬክተር) አቶ ተፈራ በየነ--

(ድምፅ)----

የዐባይ ተፋሰስ አገሮች የሚንስትሮች ም/ቤት ልዩ ስብሰባ በቅርቡ የሚካሄድ መሆኑን የገለጡት ዳንኤል ሜቦያ፣ የአንገራጋሪዎቹ አገሮች አቋም ፣ አሁን አዲስ የሽግግር አስተዳደር የመሰረተችው ግብፅ ጭምር ሊታወቅ እንደሚችል ጠቁመዋል። ከ 6 ወር ገደማ በኋላ፣ ነጻነት ታውጃለች  ተብላ የምትጠበቀው ደቡብ ሱዳን ምን አቋም እንደሚኖራት የሰጠችው ፍንጭ ይኖር ይሆን?--አሁንም ዳንኤል ሜቦያ---

«እስካሁን ምንም ዓይነት ምልክትም ሆነ ፍንጭ አላገኘንም። ስለደቡብ ሱዳን ለጊዜው ብዙም የምንለው የለም። እስከ ሐምሌ ፤ አገሪቱ ሙሉ-በሙሉ ነጻ መሆኗን እስክታውጅ ጠብቀን መመልከቱ ሳይሻል አይቀርም። ለጊዜው የዐባይን ተፋሰስ አገሮች ማኅበር እንቅሥቃሤ በተመለከተ ከደቡብ ሱዳን ዜናም  ሆነ መረጃ የለንም። ስለዚህ መጠበቅ ይኖርብናል።»

ቡሩንዲ  ውል በመፈረሟ፤ ለኢትዮጵያ ያለው ጠቀሜታ እንዴት ይገመገማል? 

(ድምፅ--አቶ ተፈራ በየነ)

ተክሌ የኋላ

ሒሩት መለሰ