1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በፈረንሳይ የቀኞቹ ድል አንድምታ

ረቡዕ፣ ኅዳር 29 2008

ፈረንሳይ ዉስጥ በተካሄደዉ የአካባቢ ምርጫ ብሔራዊ ግንባር የተሰኘዉ ፓርቲ ድል ማግኘቱ አጋጣሚ አይደለም። በሌሎች የአዉሮጳ ሃገራትም የቀኝ ክንፍ አክራሪዎች እና የአዉሮጳ ኅብረት ተቺዎች ተበራክተዉ መንቀሳቀስ ጀምረዋል። አስገራሚዉ ነገር፤ የስደተኞች ችግር እየተባባሰ በሄደ መጠን ቀኞቹ መጠናከራቸዉ መታየቱ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1HJSn
Frankreich Front National-Kandidat Fabien Engelmann
ምስል picture-alliance/dpa

[No title]

ለስደተኛ ቀዉስ መባባስ የአዉሮጳ ፖለቲከኞች በጋራ መፍትሄ እያጡለት በሄዱ መጠን የአዉሮጳ ኅብረተሰብም ችግሩ ላይ እንዲያተኩር ተገድዷል። ይህም ቀኝ ክንፍ ፖለቲከኞች ማለትም እንደፈረንሳዩ ብሔራዊ ግንባር፤ በፖላንድ ብሔራዊ ወግ አጥባቂ ፓርቲ፤ በኔዘርላንድ ደግሞ የቀኝ ፖለቲካ አራማጁ ጌርት ቪልደርስ የመራጮችን ድምፅ እንዲወስዱ ማድረጉ እየታየ ነዉ። ቀደም ብለዉ በርካታ የአዉሮጳ ፖለቲከኞች ይህን ለመቀበል ቢያዳታቸዉም አሁን እዉነታዉና መዘዙ ግልፅ የሆነላቸዉ ይመስላል።

Slowenien baut Zaun an der Grenze zu Kroatien
የስሎቫኪያ የድንበር አጥርምስል Reuters/S. Zivulovic

«የስደተኞችን ችግር ለመቆጣጠር በቀጣይ ቀናት እና ሳምንታት ተጨባጭ መፍትሄ ማምጣት ካልቻልን የአዉሮፓ ኅብረት መበታተን ይጀምራል ብዬ አምናለሁ።»

ይላሉ የስሎቫኪያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሜሮር ሴራ። ስሎቬንያ እንደሀንጋሪ ከክሮሺያ ጋር በሚያገናኛት ድንበር ላይ አጥር እየገነባች ነዉ። የአጥር ግንባታዉ በአዉሮጳ ኅብረት ተቀባይነት የሌለዉ ቢሆንም የቀኝ ፖለቲካ አራማጆቹ ግን አጥበቁ ይሹታል። ኦስትሪያ በበኩሏ በየቀኑ ወደሀገሯ እንዲገቡ የምትፈቅደዉ ስደተኞች ቁጥር የተወሰነ እንዲሆን ትፈልጋለች። በዚህም የሀገሪቱ የቀኝ ክንፍ ፓርቲ ነጥብ ማስመዝገብ ይችላል። ኦስትሪያ የምትመልሰዉ የስደተኛ ጎርፍ ያጥለቀለቃት ትንሽቱ ስሎቬኒያ ከአቅም በላይ ሆኖባታል። በዚህ ምክንያትም አንዱ ሌላዉን ሀገር ተከትሎ አጥር እገነባለሁ ድንበሬን እቆጠጣራለሁ እያለ ነዉ። የሸንገን ዉል ያልተፈራረመችዉ ብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካምሮን የድንበር ቁጥጥሩ እንደሚያስፈልጋቸዉ በድጋሚ ተናግረዋል።

«የሸንገን የድንበር ስምምነት አባል ባለመሆናችን አንገደድም፤ የድንበር ቁጥጥራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን። ይህ ለእኛ ኑሮ ደህንነት እጅግ አስፈላጊ ነዉ።»

Mazedonien baut an griechischer Grenze meterhohen Zaun
የሜቄዶኒያ ድንበር ላይ አጥርምስል picture-alliance/dpa/N. Batev

የአዉሮጳ ኅብረት በስደተኞች መበራከት ግራ ቢጋባም ድንበር አልፈዉ እንዳይመጡ ከቱርክ ጋር ተባብሮ መሥራት የሚለዉን የሚቃወሙ አልጠፉም። የሊቱዋኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳሊያ ግሪባዉስካይተ እንዲህ ነዉ ያሉት፤

«ከቱርክ ጋር በመሥራት ቱርክን መርዳት የሚለዉ አይሆንም ይህ የእኛ ኃላፊነት አይደለም።»

የአዉሮጳን አንድነት ይደግፉ የነበሩት መንግሥታት ጀርባቸዉን በማዞራቸዉም የቀኝ ክንፍ ፖለቲከኞች የተሰናዳላቸዉን መድረክ እየተቆጣጠሩ ነዉ። ስሎቫኪ እና ሀንጋሪ የአዉሮፓ ኅብረት ሃገራት 120 ሺህ ስደተኞች ወደአባል ሃገራት ይከፋፈላሉ ያለዉን በመቃወም አቤታቸዉን ለኅብረቱ ፍርድ ቤት አቅርበዋል። ቼክ ሪፑብሊክ ሮማንያ፣ ስሎቫኪያ እና ፖላንድ በጋራ የኅብረቱን የስደተኞች ፖሊስን በመቃወም ለሚያደርጉት እንቅስቃሴም የቀኝ ክንፍ ፖለቲካ አራማጆችን ድጋፍ እያገኙ ነዉ። መንግሥት የለወጠችዉ ፖላንድ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ከአሁኑ 100 ሺህ ሶርያዉያን በርሊን ላይ ቡና ሲጠጡ የእኛን ጦር ወደሶርያ ልንልክ ነዉ ወይ? የሚል ጥያቄ አቅርበዋል። ግፊት የጠናባቸዉ የአዉሮጳ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ከ18 ወራት የሙከራ ጊዜ በኋላ የስደተኞችን ጎርፍ ለመግታት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። አባባላቸዉ በአዉሮጳ የሃሳብ ለዉጥ መኖሩን ያመላክታል ተብሏል።

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ