1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በፀሐይ ኃይል የሚሠራ ዉኃ መሳቢያ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 23 2009

ከሠሃራ በስተደቡብ የሚገኙ እና ለድርቅ ተጋላጭ የሆኑ የአፍሪቃ ሃገራት በፀሐይ ኃይል የሚሠራ አዲሱ የዉኃ  መሳቢያ ሞተር ሁነኛ መፍትሄያቸዉ ነዉ ተባለ።

https://p.dw.com/p/2S2dI
Altes Windrad Flash-Galerie
ምስል AP

Beri. Washngton (US Solar water pump for Africa) - MP3-Stereo

ዩናይትድ ስቴትስ ለሰባት የአካባቢዉ ሃገራት አነስተኛ ማሳ ላላቸዉ አርሶ አደሮች በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረበች ነዉ ቢባልም ከአፍሪቃ አርሶ አደሮች አቅም አንጻር የማይቀመስ ነዉ፤ የአንዱ ሞተር ዋጋ 2,400 የአሜሪካን ዶላር በመሆኑ ይባላል።ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ግን የአካባቢዉ ሃገራት ለዚህ ጉዳይ የሚመች የፖሊሲ ለዉጥ እና የብድር አገልግሎት ለአርሶ አደሩ ካመቻቹ ድርቅን ለመከላከል ፍቱን መድኃኒት ይላሉ። ዝርዝሩን መክብብ ሸዋ ከዋሽንግተን ዲሲ ልኮልናል።

መክብብ ሸዋ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ