1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጸረ-ሽብር ሕጉ የተከሰሱ ይፈቱ ይሆን?

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 27 2010

«ክሳቸው ተቋርጦ እንደዚሁም ደግሞ የምሕረት ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት ምሕረት ተደርጎላቸው» ይፈታሉ ከተባሉት መካከል በአወዛጋቢው የጸረ-ሽብር ሕግ የተከሰሱ ይኖሩ ይሆን?

https://p.dw.com/p/2qPtx
Äthiopien kündigt Freilassung politischer Gefangenen an | Hailemariam Desalegn
Desalegn
ምስል picture alliance/AA/E. Hamid

ምኅረት እና የጸረ-ሽብር ተከሳሾች

ተቺዎቹን እና ተቃዋሚዎቹን ያስራል፤ ያሳድዳል እየተባለ የሚወቀሰው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) እስረኞችን ሊፈታ መዘጋጀቱን አስታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ እንዳሉት የሚፈቱት «በፈጸሙት ወንጀል ምክንያት በፍርድ ቤት የተፈረደባቸው ወይም ደግሞ በአቃቤ-ሕግ ክስ የተመሰረተባቸው እና ጉዳያቸው እየተጣራ የሚገኙ የፖለቲካ አመራሮች ሆነ ግለሰቦች» ናቸው።

«የተሻለ አገራዊ መግባባት ለመፍጠር ሲባል» ከእስር የሚፈቱት ግለሰቦች ማንነትም ሆነ ብዛት እስካሁን በይፋ አልተገለጠም። «አንዳንዶቹ ክሳቸውም ተቋርጦ እንደዚሁም ደግሞ የምሕረት ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት ምሕረት ተደርጎላቸው» ከሚፈቱት መካከል በአወዛጋቢው የጸረ-ሽብር ሕግ የተከሰሱ ይኖሩ ይሆን? የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የሕግ ባለሙያ ተማም አባቡልጉን አነጋግሯቸዋል። 

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ