በጥንታዊት ኢትዮጽያ የቀጭኑ ሽቦ መገናኛ
ሰኞ፣ ኅዳር 2 2000ማስታወቂያ
የዛሪ 165 አመት ግድም በአለማችን ብቅ ያለዉ ቴክኖሎጂ በአሁን ወቅት በአለም ዙርያ እየሰጠ ያለዉ ግልጋሎት በጣም የሚደነቅ አድርጎታል። በተንቀሳቃሹ ስልክ በሞባይል የተፈለገዉን ሰዉ ማግኘት አልያም የጹሁፍ መልክት ሁሉ ማስተላለፍ ተችሎአል። አፍሪቃ የሞባይል ስልክ መናሃርያ ሆናለች የሚሉ መጣጥፎችም በምዕራባዉያኑ አለም ጋዜጦች አበይት ርእስ ሆኖ መዉጣት ከጀመረ ሰንበበት አለ። በአዉሮፓ የሚኖሩ ኬንያዉያን በኬንያ የሚኖሩና የባንክ መዝገብ ለሌላቸዉ ዘመዶቻቸዉ ገንዘብ የሚያስተላልፉት በጀታ ስልካቸዉ መልክት በማስተላለፍ ነዉ፣ በኬንያ ያለዉ የተንቀሳቃሽ ስልክ ድርጅት ይህንን አገልግሎት መስጠት ጀምሮአል የሚለዉ የሳምንቱ ትኩሱ ስልክ ነክ ዜናም ነበር። በአገራችን ስላለዉ ስለ ቀጭኑ ሽቦ የስልክ አመጣጥ ታሪክ ከጥንታዊዉ ባህል እና የኑሮ ዘይቤ ጋር በማጣጣም የባህል መድረኩ ሊያሳየን ተዘጋጅቶአል መልካም ቆይታ።