1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጥበብ እንኑር

ሐሙስ፣ መጋቢት 27 2004

በዩናይትድ ስቴትስ ዋሽንግተን አካባቢ በጥበብ እንኑር በተሰኘ የኪነ-ጥበብ የመድረክ ዝግጅት ላይ አጫጭር ድራማዎች ቧልታይ ተዉኔት፣ ስነ-ቃል፣ በመድረክ ዉይይት፣ የማስንቆ ሙዚቃ ምሽት፣ ታላቅ ባህላዊ መድረክ በርካታ ኢትዮጵያዉያን አስደምሞአል።

https://p.dw.com/p/14YLP
ምስል DW

በዩናይትድ ስቴትስ ዋሽንግተን አካባቢ በጥበብ እንኑር በተሰኘ የኪነ-ጥበብ የመድረክ ዝግጅት ላይ አጫጭር ድራማዎች ቧልታይ ተዉኔት፣ ስነ-ቃል፣ በመድረክ ዉይይት፣ የማስንቆ ሙዚቃ ምሽት፣ ታላቅ ባህላዊ መድረክ በርካታ ኢትዮጵያዉያን አስደምሞአል።

ዝግጅቱ በመድረክ የቅርቡ ተዋንያን እና እድምተኞችን ብቻ ሳይሆን ያሳተፈዉ፣ በአለም ዙርያ የሚገኙ ገጣምያን ኢትዮጵያን ፖየትሪ ማለት የኢትዮጵያዉያን የስነ-ግጥም ስብስብ የፊስ ቡክ ገጽ ባወጣዉ የግጥም ዉድድር ላይ ተሳትፈዉ በጥበብ እንኑር መድረክ አንዱ አካል ነበሩ። በዚህም የስነ-ግጥም አሸናፊ ለሆኑት ከአንድ እስከ ሶስተኛ የስም ዝርዝር ይፋ ሲሆን፣ በ ስነግጥሙ የተማረኩ ተደራስያን ሽልማቱን ከኪሳቸዉ በመሸለም ይበል ቀጥሉ ሲሉ ማበረታታቸዉ ተገልጾአል። በዕለቱ ዝግጅታችን በዋሽንግተን ዲሲ ስለቀረበዉ የኪነ-ጥበብ ዝግጅት እና እንደምታዉ፣ እንዲሁም አሸናፊዎችን አነጋግረናል።

በአለም ዙርያ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ገጣሚዎች በጥበብ እንኑር በተሰኝዉ መድረክ በግጥም እንዲወዳደሩ ሃሳብን ይዘዉ የተነሱት በዋሽንግተን ዲሲ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሳምሶን ደምሴ ተፈራ ኢትዮጵያን ፖየትሪ በተሰኝዉ የፊስ ቡክ ገጽ ላይ ኢትዮጵያዊ ባህልን ገላጭ የሆነ ስዕልን በመለጠፍ ገጣምያን ለዉድድሩ ጋበዙ። ስዕሉ አንድ ምርኩዝ የያዘ ባለ ቁምጣ የገጠር ወጣት በባዶ ግሩ ከበግ ፀጉር የተሰራ ቆቡን አጥልቆ አንገት ልብሱን ተከናንቦ ምርኩዙን ተደግፎ በሚኖረበት ገጠር ለጥ ያለ ሜዳ ላይ እዝያ ማዶ እያየ በሃሳብ ተዉጦአል። ይህን ስዕል አይቶ ልቡ ያለዉን በተባ ብዕሩ ያስቀመጠዉ የአዲስ አበባዉ ነዋሪ የ26 አመት ወጣት ዳኜ አሰፋ በብዕር ስሙ «የየዉብዳር ልጅ» በኤሌክትሮኒክሱ የማህበረሰብ መገናኛ ገጽ ከምድረ አማሪካ አድርሶ የተደራሲዉን የበጥበብ እንኑርን ዳኞች ልብ ኮረኮረ! ሙሉዉን ቅንብር አዳምጡ!

አዜብ ታደሰ

ሸዋዪ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ