1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በግብፅ የምክር ቤት ምርጫና ውዝግቡ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 21 2003

ከትናንት በስትያ በግብፅ የተካሄደው የምክር ቤት ምርጫ ማጭበርበር እንደተከሰተበት ተቃዋሚዎች ገለፁ። ሁኔታዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ በምክር ቤቱ ምርጫ የፕሬዚዳንት ሆስኒ ሞባረክ ፓርቲ ከፍተኛ መቀመጫ እንደሚያገኝ ተገምቷል። ተቃዋሚዎች ውጤቱን እንደማይቀበሉት እየዛቱ ነው። ማንተጋፍቶት ስለሺ ዝርዝር ዘገባ አጠናቅሯል።

https://p.dw.com/p/QLM9
በግብፅ ፖሊስ ሁለት መራጮችን ሲያግድ
በግብፅ ፖሊስ ሁለት መራጮችን ሲያግድምስል DW

ከትናንት በስተያ በግብፅ በተካሄደው የምክር ቤት ምርጫ ተቃዋሚዎች እንግልት እንደተፈጸመባቸው ገለፁ። በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች ድብደባ ጭምር እንደነበረም ተዘግቧል። በተለይ በወደብ ከተማይቱ አሌክዛንደሪያ የተቃዋሚ ፓርቲ የምርጫ ታዛቢዎች በምርጫ ጣቢያ እንዳይገቡ መታገዳቸውም ተጠቅሷል። በግብፅ ዋነኛው የተቃዋሚ ፓርቲ እንደሆነ የሚነገርለት ሙስሊም ወንድማማችነት ፓርቲ ምርጫው የተጭበረበረና ተቀባይነት የሌለው ነው ሲል ትናንት አስታውቋል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ
አርያም ተክሌ