ከአሜሪካን የተባረሩት ኢትዮጵያዊ ጉዳይ
ሐሙስ፣ መጋቢት 21 2009ማስታወቂያ
በዩናይትድ ስቴትስ አትላንታ ፌደራዊ ክፍለ ሀገር ነዋሪ የነበሩ አንድ ኢትዮጵያዊ ሴት ልጃቸውን ገርዘዋል ተብለው የተፈርደባቸውን የአሥር ዓመት እሥራት ከጨረሱ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ መባረራቸው ተዘግቧል ። ከአሜሪካ የስደተኖች ጉዳይ ጽህፈት ቤት በተገኘው መረጃ መሠረት ከጎርጎሮሳዊው 2003 ዓም ወዲህ በተመሳሳይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል የተጠረጠሩ 380 ያህል ሰዎች ሲታሰሩ 785 ደግሞ ከአሜሪካ ተባረዋል ።
መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ