በግልገል ጊቤ ግድብ ላይ ተቃውሞና የመብራት ኃይል መግለጫ፣
ሐሙስ፣ ግንቦት 13 2001ማስታወቂያ
ይህን ተቃውሞአቸውን ያሰሙት ፣ በቅርቡ፣ የአፍሪቃ ልማት ባንክ፣ ዳካር፣ ሴናጋል ውስጥ ዓመታዊ ጉባዔውን ባካሄደበት ወቅት እንደነበረ ታውቋል። የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ድርጅት፣ እንደሚነገረው፣ በ 17 ቢልዮን ብር እያስገነባው ያለውና 1,870 ሜጋ ዋት ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጨው የግልገል ጊቤ ቁ 3፣ ፕሮጀክት፣ 32 ከመቶ ሥራው ተጠናቋል ሲል ድርጅቱ አስታውቋል። የመብራትኃይሉ ድርጅት፣ ግድቡ፣ ለአካባቢው ኑዋሪዎችና ለብዝኅ-ህይወት አደጋ ይኖረዋል በማለት ፣ የውጭ አበዳሪዎች፣ የሚሰጡትን ብድር ለጊዜው አግደዋል ተብሎ የተወራው ስህተት ነው ሲል ለ ዶቸ ቨለ ግልጿል። አበበ ፈለቀ፣ ከዋሽንግተን ዲ ሲ፣እንዲሁም ታደሰ እንግዳው ከአዲስ አበባ ተከታዮቹን ዘገባዎች አጠናቅረዋል።
ተክሌ የኋላ፣
ሒሩት መለሰ፣