1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በደቡብ አፍሪቃ ኢትዮዽያውያን ላይ የደረሰው የግድያ ጥቃት

ሐሙስ፣ ሐምሌ 29 2002

ግድያው ከዜኖፎቢያ ጋር የተያያዘ አይደለም ይላል ፖሊስ። በክስተቱ በደቡብ አፍሪካ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮዽያውን ተደናግጠዋል።

https://p.dw.com/p/Od4s
በደቡብ አፍሪቃ ኢትዮዽያውያን ላይ የደረሰው የግድያ ጥቃት
ምስል AP

በቅርቡ በደቡቡ አፍሪካ ነዋሪ የሆኑ 3 ኢትዮዽያውያን ባልታወቁ ሰዎች ተገድለዋል። በተለያዩ ቀናት የተገደሉት እነዚህ ኢትዮዽያውያንን በተመለከተ የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ የተጠናከረ ምርመራ እያደረገ ቢሆንም ክስተቱ ኢትዮዽያውያንን ያስደነገጠ ሆኗል። ጉዳዩ ከዜኖፎቢያ ጋር ስለመያያዙ ማረጋገጫ ባይገኝም ፖሊስ የወንጀል ተግባር እንደሆነ ገልጿል። ጉዳዩ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው። በዓለም ዋንጫ ስኬቷ ከተወደሰችው ደቡብ አፍሪካ ይህ ዜና መሰማቱ በሀገሪቱ ወንጀል እየጨመረ እንደመጣ የሚያሳይ ክስተት ነው። መሳይ መኮንን በጉዳዩ ዙሪያ አንድ በደቡብ አፍሪካ ነዋሪ የሆነ ኢትዮዽያዊንና የፖሊሲ ቃለአቀባይ አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ አዘጋጅቷል።

መሳይ መኮንን

አርያም ተክሌ