የመን እና ውጊያው
ሰኞ፣ ጥር 15 2009ማስታወቂያ
አንዳንድ የውጭ ዜና ምንጮች የየመን መንግሥት ጦር በቀይ ባህር ጠረፍ የሚገኘውን የሞካን ግዛት ከዓማፅያኑ እንዳስለቀቀ ሲዘግቡ ተሰምቷል። የመንግሥቱ ጦር ከሁለት ሳምንታት በፊት በቀይ ባህር እና በኤደን ባህረ ሰላጤ መካከል የሚገኘውን ስልታዊውን የባብ ኤል መንደብ መተላለፊያ መልሶ በተቆጣጠረበት ጊዜ ነበር የሁቲ ዓማፃያን ወደ ሞካ ግዛት ያፈገፈጉት።
የመን ውስጥ ከመስከረም 2014 ዓም ወዲህ የርስበርስ ጦርነት እንደቀጠለ ነው። በተመድ ዘገባ መሰረት፣ ከመጋቢት 2015 ዓም ወዲህ የሳውዲ ዓረቢያ መራሹ የዓረብ ሃገራት ወታደራዊ ቅንጅት በሁቲ አንፃር ጥቃት ማካሄድ ከጀመረ ወዲህ 7,000 ሰዎች፣ ብዙ ሲቭሎች ተገድለዋል፣ ሶስት ሚልዮን ደግሞ ሸሽተዋል።
ግሩም ተክለማርያም/አርያም ተክሌ
አዜብ ታደሰ