በዚምባብዌ የኮሌራ ወረርሽኝ የመባባሱ ስጋት27 ታኅሣሥ 2001ሰኞ፣ ታኅሣሥ 27 2001በዚምባብዌ በአውሮፓውያኑ 2009 ዓመተ ምህረት በኮሌራ የሚያዙት ሰዎች ቁጥር በዕጥፍ ያድጋል ተብሎ ይገመታል ።https://p.dw.com/p/GSOMምስል APማስታወቂያበዚምባብዌ በንፁህ የመጠጥ ውሀ ዕጥረት ሳቢያ ስለተከሰተው የኮሌራ ወረረሽኝ ሙጋቤ እና ረዳቶቻቸው አላላውስ ያሏቸው የሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች እንኳን ብዙም የሚያውቁት የለም ። የሙጋቤ ምስጢራዊ የደህንነት አባላት የኮሌራ ወረርሽኝ እጅግ የተስፋፋባቸው አካባቢዎች እንዳይታዩ ከልለዋል ።