በዓለም የጦር ወንጀለኛ ፍርድ ቤት እና የአፍሪቃዉያን አመለካከት
ማክሰኞ፣ ጳጉሜን 5 2005ማስታወቂያ
ከ 1,000 በላይ ኬንያውያን መገደላቸውና ከ 600,000 በላይ ህዝብ ከቀየው መፈናቀሉን ተከትሎ፤ የዓለም ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መርማሪ ፍርድ ቤት፤ ፕሬዚዳንት ዑሑሩ ኬንያ እና ምክትል ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ በተፈጠረው ሁከትና ግድያን አቀነባብረዉ፤ በሰብዓዊነት ላይ ወንጀል ፈጽመዋል ሲል ክስ ማቅረቡ ይታወቃል። ከዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መርማሪ ፍርድ ቤት የመዉጣት ዉሳኔን የኬንያ መንግስት ብቻ ማፅደቅ ቢችልም ቅሉ ባሳለፍነዉ ሳምንት የኬንያዉ ምክር ቤት ሀገሪቱ ከ ICC እንድትወጣ በውሳኔ ከደገፈ በኋላ፤ የICC አባል ሀገር የሆነችዉ ዩጋንዳ፤ የኬንያን ምክር ቤት ዉሳኔ አወድሳለች። ይህ የዩጋንዳ አቋም ምንን ያመለክታል፤ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ መምህር የሆኑት የህግ ባለሞያዉ ዶክተር ያዕቆብ ኃይለማርያ ይመልሱልናል፤
አዜብ ታደሰ
ተክሌ የኋላ