1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሠልፎች

ሰኞ፣ የካቲት 23 2001

ፕሬዚዳንት ኦባማ፣ የአሜሪካን አስተዳደር ታሪክ ከጎናችሁ ነው። በአፍሪቃ ለሚፈፀመው የሠብአዊ ጥሰት አይሆንም በሉ። ብርቱካን ሚደቅሳ ትፈታ፣ ቴዲ አፍሮ ይፈታ፣ በኢትዮጵያ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ ይፈቱ ሲሉም ድምፃቸውን አሰምተዋል።

https://p.dw.com/p/H4AT
ምስል AP GraphicsBank/DW
በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሰኞ በብሪታንያ፣ በስዊድን፣ በኖርዌይና በስዊዘርላንድ መዲናዎች የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸውን፤ ማምሻውን በዩኤስ ዋሽንግተን ዲሲ እንደሚያደርጉም አስተባባሪዎቹ ገለፁ። የፍትህና አንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱ ካንሚደቅሳ፣ አርቲስት ቴዲ አፍሮና ሌሎች የፖለቲካ እስረኞችም እንዲፈቱ፣ በሀገሪሪቱ የሠብዓዊ መብት እንዲከበር ሠልፈኞቹ ጥሪ አድርገዋል። የተቃውሞ ሠልፎቹ የሚደረጉት በአሜ ሪካን ኤምባሲዎች ደጃፍ መሆኑም ታውቓል።