በዉጭ የሚገኙ የኢትዮጵያን ቅርሶች ለማስመለስ ጥረት
ሰኞ፣ ኅዳር 6 2008ማስታወቂያ
በመክፈቻዉ ሥነ-ስርዓት ላይ የኤጀንሲዉ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብርኃም ጦሳ ስለ ኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርሶች ንግግር አድርገዋል። ኢትዮጵያ በረጅም የታሪክ ዘመንዋ ያሰባሰበችዉ የማንነትዋ መለያ የሆኑ በዉቅ የተሰሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ብርቅዬ ቅርሳ ቅርሶችዋ በተለያዩ ጊዚያት ከሀገር የወጡ በመሆናቸዉ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደደረሰም ተመልክቶአል። አሁንም በሀገሪቱ ዉስጥ የሚገኙት ጥንታዊ ቅርሶች በሕገ-ወጥ እጅ ገብተዉ በተለያዩ መንገዶች ወደ ዉጭ ሃገራት እንዳይወጡ፤ ለሽያጭ እንዳይዉሉ መንግስት ቁጥጥር ማድረግ እንዳለበት ተመልክቶአል ። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ፤ ባለሞያዎችንና ያገባናል ያሉ አንዳንድ ሰዎችን አነጋግሮ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ