1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«በወጣትነት ያባከንኳት ጊዜ»- አቤሰሎም አርዓያ

ቅዳሜ፣ ግንቦት 9 2006

ወጣትነት ከመቼውም ጊዜ በላይ በርካቶች ሱስ የሚያሲይዙ ነገሮች ለመሞከር የሚፈተኑበት ጊዜ ነው። ከገቡበት ደግሞ ፤ የቻሉ በራሳቸው ኃይል ያልቻሉ ደግሞ እድሜ ልካቸውን ለሱስ አስያዦች ጥገኛ ሆነው ይቀራሉ። የዛሬው የወጣቶች ዓለም እንግዳችን ራሱን ከሱሰኝነት አላቋል። ልደት አበበ አነጋግራዋለች።

https://p.dw.com/p/1C0tb
Symbolbild Rauchen
ምስል Fotolia/ Gina Sanders

አቤሰሎም አርዓያ ይባላል። ዛሬ ወጣት አይደለም። የወጣትነት ጊዜውን ግን በደንብ ያስታውሳል። በወጣትነቱ ስላባከነው እና ከመንገድ ስለወጣበት ጊዜ ገልፆልናል።

ጭንቀት ወይም ስራ ማጣት ወጣቶች ሱሰኛ ከሚሆኑባቸው ምክንያቶች ጥቂቶቹ ናቸው። ከዛ ደግሞ በራስ አነሳሽነት? ወይስ በሌሎች ሰዎች ግፊት? የሚለው ጥያቄም አለ፤ የአቤሰሎምምክንያቱ ሁለቱም ነበር። አቤሰሎምእንደቀልድ የጀመረው ሱስ ሆኖ ከዕለት ከዕለት ህይወቱ መለየት የማይታሰብ ደረጃ ላይ ደርሶ ነበር። ምንም እንኳን አደባባይ ተቀምጦ ጫት ባይቅምና ሲጋራ ባያጨስም፤ በወቅቱ ሱሰኛነቱ የሚያውቁ ፤እንዲተውም የመከሩትም አልጠፉም።አቤሰሎምእድለኛ ነው። ከገባበት ሱስ ራሱ ባኖ ለመውጣት ብዙ ጊዜ አልፈጀበትም። የገጠመው ከፍተኛ ሀዘን ከሱሱ አላቆታል።

Symbolbild Rausch Mann Alkohol Zigarette Kater trinken betrunken
ምስል picture-alliance/dpa

አቤሰሎም ከመጠጥ፣ ሲጋራ እና ጫት ያለፈ ሌሎች አደንዛዥ እፆች እንዳልወሰደ ገልፆልናል። ቢሆንም እስከመቼ እንደዚህ እቀጥላለሁ ሲል ራሱን የጠየቀው አቤሰሎም ሁሉን ነገር ርግፍ አድርጎ ለመተው ቢወስንም፤ መጀመሪያ ላይ ከብዶት ነበር።ዛሬ አቤሰሎም ተቀይሯል።በእድሜም ከጎልማሶቹ ይቆጠራል። « አርባን ማየት ጀምሬያለሁ» ይላል። ዛሬ በፊልም ስራ የተሰማራው አቤሰሎም አርዓያ ፤በወጣትነት በሱስ ስላባከነው ጊዜ አጫውቶናል።

ለበለጠ የድምጽ ዘገባውን ከፍተው ዝግጅቱን ይስሙ።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ