1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሪያድ የኢትዮጵያዉያን አስተያየት

ዓርብ፣ ጥቅምት 11 2009

የኢትዮጵያ መንግሥት ያወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና ዝርዝር መመሪያዎቹ ገዢው ፓርቲ ለበርካታ ዓመታት ሲተገብራቸው የኖሩትን ተግባራት ሕጋዊ ለማሰኘት ተብለው የወጡ እንጂ እንደ አዲስ ሊታዩ ይገባቸዋል ብለው እንደማያምኑ አስተያየታቸውን የሰጡ የሪያድ ነዋሪ ኢትዮጵያዊያን ገለጹ።

https://p.dw.com/p/2RXHF
Äthiopien Protest
ምስል Reuters/T. Negeri

Ethio. in Riyadh Opinion on the Current political situation - MP3-Stereo

 እንደ አስተያየት ሰጪዎቹ እምነት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም ሆነ የአፈጻጸም መመሪያው መንግሥት ያመጡልኛል ከሚላቸው መረጋጋቶች ይልቅ ማኅበራዊ መናጋቶችን፤ ከሰላም ይልቅ ቀውስን የሚጋብዙ ናቸው። እንደነሱም አዋጁ ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ እንደ ፓርቲም ሆነ እንደ መንግሥት ለዓመታት በመልካም ገጽታ ግንባታ በተለይም በዲፕሎማሲዉ መስክ አምጥቻቸዋለሁ በሚለው ስኬቶች ላይ ውኃ የመቸለስ ያህል ነው። ስለሺ ሽብሩ ከሪያድ   ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።

ስለሺ ሽብሩ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ