በካምፓላ የተፈጸመው የቦምብ ጥቃት
ሰኞ፣ ሐምሌ 5 2002ማስታወቂያ
ትላንት ምሽት የዓለም ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታን ለመመልከት ካምፓላ በሚገኙት የራግቢ ስፖርት ክበብ እና በኢትዮዽያ ሬስቶራንት የተለያዩ ሃገራት ዜጎች ታድመዋል። ድንገት ግን ከፍተኛ የሆነ ፍንዳታ ተሰማ። በሁለቱም ቦታዎች የፈነዱት ቦምቦች ወዲያውኑ የ64 ሰዎችን ህይወት አጠፋ። በመቶዎች የሚቆጠሩት ክፉኛ ቆሰሉ። ፖሊስ እንዳለው ጥቃቱን የአልሸባብ ቡድን ሳይፈጽመው አይቀርም። በኢትዮዽያ ሬስቶራንት በደረሰው ጥቃት 10 ኢትዮዽያውያንና ኤርትራውያን ህይወታቸውን አጥተዋል።
መሳይ መኮንን
ተክሌ የኋላ