በኦንግ ሳን ሱ ቺ ላይ የተላለፈው ብይን
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 5 2001ማስታወቂያ
የሀገሪቱ ፍርድ ቤት በይኖት የነበረውን የሶስት ዓመት እስራት ከጉልበት ስራ ጋር ቅጣትን የሀገሪቱ ወታደራዊ መሪ ጀነራል ታንሹዊ ዛሬ ወደአስራ ስምንት ወራት እስራት ቀየሩት። ኦንግ ሳን ሱ ቺ በቁም እስር እያሉ ህግ በመጣስ አንድ አሜሪካዊ በዋና ወደ መኖሪያ ቤታቸው እንዲገባ ፈቅደዋል በሚል ነበር ክስ የተመሰረተባቸው። ካለፉት አስራ አራት ዓመት ወዲህ በቁም እስር የሚገኙት የኖቤል ሰላም ተሸላሚዋ ኦንግ ሳን ሱ ቺ ላይ የተላለፈው ብይን ዓለም አቀፍ ወቀሳ አፈራርቆዋል፤ የአውሮጳ ህብረትም በዚችው ሀገር ላይ ያሳረፈውን ማዕቀብ እንደሚያጠናክር አስታውቋል።
ይልማ ሀይለሚካኤል/አርያም ተክሌ/ሸዋዬ ለገሠ