1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በእየሩሳሌም ሙክራብ ላይ የደረሰ ጥቃት

ማክሰኞ፣ ኅዳር 9 2007

በየእሩሳሌም ሙክራብ ላይ የደረሰ ጥቃትእየሩሳሌም ውስጥ የተነሳው ብጥብጥ ይበልጥ ከሯል። ዛሬ ዳግም አዲስ ጥቃት ከተማዋን አናግቷል። ይህም በአይሁዳውያን ቤተ ፀሎት ላይ ነው። በዚህም ጥቃት 6 ሰዎች ሰዎች ተገድለዋል። ሁለት ጥቃት አድራሾች እና አራት ሲቪሎች።

https://p.dw.com/p/1DpMZ
Anschlag auf eine Synagoge in Jerusalem 18.11.2014
ምስል Reuters/R. Zvulun

ጥቃት አድራሾቹ ዕድሜያቸው በ20ቹ መጀመሪያ ላይ የሚገኝ ፍልስጤማውያን ናቸው ተብሏል። ምስራቅ እየሩሳሌም ውስጥ ከሚገኝ ጃበል ሙካበር ከተባለ ከተማ። ቢሊዋ ፣ መጥረቢያ እና ጠመንጃ ተጠቅመው ነው ሁለቱ ወጣቶች በአይሁዶች ቤተ መቅደስ ላይ ደም ያፋሰሱት። ወጣቶቹ ከፖሊስ በተከፈተ ተኩስ ተገድለዋል። ከዚህ ጥቃት በኋላ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔትናያሁ እስራኤል ጠንከር ያለ ርምጃ እንደምትወስድ አስታውቀዋል። ወጣቶቹ ጥቃቱን ለምን አደረሱ ስለሚለው ብዙም የሚጠይቅ የለም። የምጣኔ ሀብት ሚኒስትር ቤኔት ለዚህ ሁሉ ተጠያቂ የሚያደርጉት ፤ አሸባሪ ብለው የሚጠሯቸውን የፍልስጤም ፕሬዚዳንት አባስ ነው።«በምናባዊዉ የመካከለኛዉ ምሥራቅ ዲፕሎማሲ ጉዳይ በተያዝንበት ወቅት ፍልስጤማዉያን በሽብርና በማነሳሳት ከበዉናል። በተቃራኒዉ ግን ሽብር እንቅፋት ነዉ የሚያስከትለዉ። አባስ እስራኤል ላይ ጦርነት አዉጀዋል፤ እናም አፀፋዉን በተገቢዉ መንገድ መመለስ አለብን።»

የቀድሞው የእየሩሳሌም የፖሊስ አዛዥ አሪ አሚትም ቢሆኑ መፍትሄው ጦርነት ነው ሲሉ ነው በእስራኤል ራዲዮ ዛሬ የተሰሙት።« ጠማንጃ ያለው ሰው ሁሉ ኪሱ ይሸጉጥ፣ የጦር መሳሪያ ፍቃዱን ደግሞ የገንዘብ ቦርሳው ውስጥ ይክተት። ፍርድ ቤት ችግር እንጋይገጥመው ማለት ነው። ያለነው ጦርነት ውስጥ ነው ስለዚህ ጦርነት ውስጥ እንዳለን አውቀን መንቀሳቀስ ይኖርበናል። ሁላችሁም ሽጉጣችሁን ይዛችሁ ፖሊሶችን ደግፉ።»

Palästina Proteste Jerusalem Westjordanland 14.11.2014
ምስል Reuters/A. Awad

ስልጣን ላይ ያሉት የፖሊስ አዛዥ ጆሀናን ዳኒኖ ግን መረጋጋትን ነው የሚጠይቁት።« ያለው ቁጭት ይገባኛል። ህመሙንም እረዳለሁ። በግልፅ ግን መናገር የምፈልገው። ስራችንን እንድንፈፅም ለኛ ተዉልን። ህጉ የማይፈቅደውን ነገር ለማድረግ አትሞክሩ። ጥቃት ለመጣል የሚያስቡት ላይ አግባብ የሆነውን ርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነን። ሁላችንም ግን አሁን መረጋጋት ይኖርብናል።»

ፖሊስ እና የሀገሩቱ የስለላ ድርጅት አደጋው የደረሰበት ቦታ ተገኝቶ ምርመራ አካሂዷል። ከዚህም በተጨማሪ የጥቃት ጣዮቹን ወላጆች በቁጥጥር ስር አውለዋል።

ክርስቲያን ቫግነር / ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ