በኤርትራ ባለሥልጣናት ላይ የቀረበው ጥቆማ ውድቅ መደረጉ
ሐሙስ፣ ሐምሌ 10 2006ማስታወቂያ
የስዊድን አቃቤ ህግ ፣የስዊድን የህግ ባለሞያዎች በስብዕና ላይ ወንጀል ፈፅመዋል ሲሉ የኤርትራውያን ባለሥልጣናትን ስም ዝርዝር ያቀረቡበትን ጥቆማ ውድቅ አደረገ ። የህግ ባለሞያዎቹ በሰብዓዊነት ላይ የተፈፀመ ወንጅል በስዊድን ህግ የሚያስጠይቅ እንዲሆን በተፈቀደበት በጎርጎሮሳውያኑ ሐምሌ 1 2014 ዓም የኤርትራው ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ና ሶስት ሚኒስትሮችን እንዲሁም አማካሪያቸው በሰብዕና ላይ ወንጀል ፈፅመዋል ሲሉ ስማቸውን ጠቁመው ነበር ። ይሁንና አቃቤ ህግ ፣ህጉ ሥራ ላይ እንዲውል ከተደረገበት እለት በኋላ የተፈፀሙ ወንጀሎችን ብቻ የሚመለከት መሆኑን ሰሞኑን በማሳወቅ ጥቆማውን ውድቅ አድርጓል ።የስቶክሆልሙ ዘጋቢያችን ቴዎeሮስ ምህረቱ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ቴዎድሮስ ምህረቱ
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ